23
Jun
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ6ኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ ቀሪ ምርጫ በሚደረግባቸው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና አፋር ክልሎች እንዲሁም ድጋሚ ምርጫ በሚደረግባቸው በጅግጅጋ 2 እና መስቃንና ማረቆ ምርጫ ክልሎች በዛሬው ዕለት ምርጫ እየተካሄደ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ በ6ኛው ዙር ሀገራዊ ቀሪና ድጋሚ ምርጫ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ ድምፅ መስጠት መጀመሩን አስታውቋል። ዛሬ እየተካሄደ ባለው የድምጽ አሰጣጥ ሂደት ላይም 12 የፖለቲካ ፓርቲዎች እየተሳተፉ መሆኑን ከምርጫ ቦርድ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ቀሪና ድጋሚ ምርጫ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በአፋር፣ በሶማሌ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች እየተካሄደ መሆኑንም ነው ቦርዱ ያስታወቀው። ቀሪና ድጋሚ ምርጫ ከሚካሄድባቸው አካባቢዎች አንዱ በአፋር ክልል የሲሆን፤ በክልሉ 4 ዞኖች፣ በ9 የምርጫ ክልሎች እና በ388 የምርጫ…