20
Nov
የብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን እንዳስታወቀው በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ጦርነት ተሳትፎ ከነበራቸው 274 ሺህ የትግራይ ተዋጊዎችን ወደ ቀድሞ ህይወታቸው እንደሚመልስ አስታውቋል፡፡ ከዚህ ውስጥም በመጀመሪያው ምዕራፍ 75ሺህ የቀድሞ ተዋጊዎችን ዲሞቢላይዝ የማድረግ ስራውን በነገው እለት በይፋ እንደሚጀመር ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡ ኮሚሽኑ ፕሮግራምና ፕሮጀክቶች በመቅረጽ ከሰባት ክልሎች ከ371 ሺህ በላይ የቀድሞ ተዋጊዎችን ከ760 ሚሊየን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ በሁለት ዓመታት ውስጥ የዲሞቢላይዜሽንና መልሶ ማቋቋም ስራውን ለመጨረስ የሚያስችል ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጿል። ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮም ለመጀመሪያው ዙር ተዋጊዎች ብተና ማስፈጸሚያ ሀብት መንግስትና ከለጋሾች ማግኘት ተችሏል ተብሏል፡፡ መንግስት ኮሚሽኑ ስራ ሲጀምር 1 ቢሊዮን ብር የተለገሰ ሲሆን በተጨማሪም ከ7 ሀገራት 60 ሚሊየን ዶላር መገኘቱ ተገልጿል። በድጋፍ የአውሮፓ…