09
Feb
የትግራይ ክልል የቀድሞ ፕሬዝዳንት ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ከአራት ዓመት በኋላ ወደ አዲስ አበባ መጡ:: ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ኢትዮጵያ ለዓመታት ወደ ጦርነት እንድተገባ የተገደደችበትን የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን እዝ እሳቸው የሚመሩት የትግራይ ልዩ ሀይል እንዲያጠቃ ማድረጋቸው አይዘነጋም፡፡ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊያን የተገደሉበት እና 28 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ ንብረት የወደመበት ይህ ጦርነት ከአንድ ዓመት በፊት በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ከተፈረመ በኋላ ቆሟል፡፡ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በዛሬው ዕለት ከአራት ዓመት በኋላ ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ የመጡ ሲሆን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር ፊት ለፊት ተገናኝተዋል፡፡ ደብረጽዮን እና ሌሎች የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ኃላፊዎች ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር በአዲስ አበባ በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አፈጻጸም…