26
Sep
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ካሳለፍነው ሰኔ ወር ጀምሮ በኢትዮጵያ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል፡፡ ኢሰመኮ በሪፖርቱ ላይ እንደጠቀሰው በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ጋምቤላ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ላይ ከህግ ውጪ ግድያ፣ የዘፈቀደ እስር፣ እገታ፣ አስገድዶ መድፈር እና ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በንጹሀን ላይ ተፈጽመዋል ብሏል፡፡ ከሰኔ ወር ጀምሮ ባሉት ሶስት ወራት ውስጥ በአማራ ክልል በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች እና ፋኖ ታጣቂዎች መካከል በተፈጠረው ጦርነት ከ160 በላይ ዜጎች መገደላቸውን ኢሰመኮ አስታውቋል፡፡ ግድያ ከተፈጸመባቸው ዜጎች መካከል የአዕምሮ ህመምተኞች፣ አዛውንቶች፣ ህጻናት እና ሴቶች እንደሚገኙበት ተገልጿል፡፡ ጎንደር፣ የጎጃም አካባቢዎች፣ ደብረሲና፣ አታዬ፣ ሸዋሮቢት እና ሌሎችም ቦታዎች ያሉ ሲሆን መረጃ ለፋኖ ትሰጣላችሁ፣ የመንግስት ጉዳይ አስፈጻሚ…