Africaunion

የአፍሪካ ህብረት በራያ እና አላማጣ የተከሰተው አዲስ ግጭት እንደሚያሳስበው ገለጸ

የአፍሪካ ህብረት በራያ እና አላማጣ የተከሰተው አዲስ ግጭት እንደሚያሳስበው ገለጸ

የአማራ እና የትግራይ ክልል የይገባኛል ጥያቄ በሚያነሱባቸው የራያ አላማጣ እና አካባቢዋ ግጭቶች መከሰታቸውን ተከትሎ የአፍሪካ ህብረት መግለጫ አውጥቷል። መግለጫው የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት በአወዛጋቢዎቹ ራያ አላማጣ፣ ዛታ እና ኦፎላ "በአካባቢው ማህበረሰብ መካከል ያሉ ውጥረቶችን" በትኩረት እየተከታተሉት መሆኑን ገልጿል። በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት በተደረሰው የፌደራል መንግስት እና የህወሓት የዘላቂ ሰላም ስምምነት፣ ሁለቱ ክልሎች የይገባኛል ጥያቄ የሚያነሱባቸው "አወዛጋቢ ቦታዎች" በህገመንግስቱ መሰረት እልባት እንዲያገኙ እንደሚደረግ ይጠቅሳል። ሊቀመንበሩ ሁለቱም ወገኖች ግጭት ከማባባስ እንዲታቀቡ እና የአካባቢውን ንጹሃን መፈናቀል እንዲያስቆሙ ጥሪ አቅርቧል። ከአፍሪካ ህብረት በተጨማሪም መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የሰባት ሀገራት ኤምባሲዎች በአማራ እና ትግራይ ከልል አዋሳኝ ቦታዎች ላይ ያጋጠመው አዲስ ግጭት እንዳሳሰባቸው አስታውቀዋል፡፡ የካናዳ፣…
Read More
አፍሪካ ህብረት በፕሪቶሪያ የተፈረመው የኢትዮጵያን የሰላም ስምምነት መገምገም ጀመረ

አፍሪካ ህብረት በፕሪቶሪያ የተፈረመው የኢትዮጵያን የሰላም ስምምነት መገምገም ጀመረ

በዚህ ግምገማ መድረክ ላይ የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት፣ ህወሃት፣ በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሀመር እና ሌሎችም ተገኝተዋል፡፡ በሰሜን ኢትዮጵያ ለሁለት ዓመታት በዘለቀው ጦርነት የአፍሪካ ህብረት በደቡብ አፍሪካ ዋና ከተማ ፕሪቶሪያ ሰላም ስምምነት ከተፈረመ በኋላ ጦርነቱ መቆሙ ይታወሳል፡፡ ይህ የሰላም ስምምነት ከተፈረመ አንድ ዓመት ያለፈው ሲሆን በስምምነቱ መሰረት ያልተፈጸሙ ጉዳዮች እንዳሉ በሁለቱም ወገኖች ሲነሳ ቆይቷል፡፡ አፍሪካ ህብረት በኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት መካከል የተደረሰውን የፕሪቶሪያ የተኩስ ማቆም ስምምነት አፈፃፀም ስትራቴጂካዊ ግምገማ እያካሄደ መሆኑን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ይፋ አድርገዋል። የትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ በኤክስ ገፃቸው ባጋሩት መልእክት የአፍሪካ ህብረት በኢትዮጵያ መንግስት እና በህዝባዊ ወያነ ሓርነት…
Read More
ማውሪታኒያ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበርነትን ከኮሞሮስ ተረከበች።

ማውሪታኒያ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበርነትን ከኮሞሮስ ተረከበች።

37ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ሲሆን የህብረቱ አባል ሀገራት መሪዎች በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡ ምዕራብ አፍሪካዊቷ ማውሪታኒያ በ2024 የአፍሪካ ህብረትን በሊቀመንበርነት እንድትመራ የተመረጠች ሲሆን የሊቀመንበርነት ቦታውን ከ2023 የህብረቱ ሊቀመንበር ከነበረችው ኮሞሮስ ተረክባለች፡፡ የማውሪታኒያ ፕሬዝደንት መሀመድ ኦዉልድ ጋዞኒ ከወቅቱ የህብረቱ ሊቀመንበር ከኮሞሮሱ ፕሬዝደንት አዛሊ አሶውማኒ ተረክበዋል። የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበርነት ስልጣን የህብረቱ አባል ሀገራት በየዓመቱ እየተቀያየሩ የሚያገኙት ስልጣን ሲሆን ከህብረቱ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጋር በመሆን ስራን ማቀላጠፍ እንዲሁም አፍሪካን የሚመለከቱ ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ የመሳተፍ ሀላፊነት አለበት፡፡ ፕሬዝደንት ኦውልድ ዛሬ የተመረጡት የህብረቱ ስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት የሆነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባለፈው ረብዕ እና ሐሙስ ዕለት ባካሄዱት ጉባኤ እንዲመረጡ ይሁንታ ከሰጣቸው…
Read More
ራይላ ኦዲንጋ ለአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበርነት እንደሚወዳደሩ ገለጹ

ራይላ ኦዲንጋ ለአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበርነት እንደሚወዳደሩ ገለጹ

ኬንያዊው ራይላ ኦዲንጋ የወቅቱ የወቅቱን የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማትን ለመተካት በሚደረገው ምርጫ ላይ መወዳደር እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡ ከፈረንጆቹ 2017 ጀምሮ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር የሆኑት ሙሳ ፋኪ መሃማት የስልጣን ጊዜያቸው የፊታችን ሐምሌ ያበቃል፡፡ ይህን ተከትሎም ሙሳ ፋኪ መሀማትን ለመተካት ሀገራት ከወዲሁ እጩዎቻቸውን እያቀረቡ ሲሆን ኬንያዊው ተቃዋሚ ፖለቲከኛ ራይላ ኦዲንጋ ለአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበርነት እንደሚወዳደሩ አስታውቀዋል፡፡ ራይላ ኦዲንጋ ለዚህ እንዲረዳቸው የቀድሞ የናይጀሪያ ፕሬዝዳንት እና የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ መልዕክተኛ ኦሊሶጎኖ ኦባሳንጆ ሀገራትን እንዲያሳምኑለት እንደመረጣቸውም ተናግሯል፡፡ የኬንያ ፕሬዝዳንት ለመሆን አራት ጊዜ ተወዳድረው የተሸነፉት ራይላ ኦዲንጋ በቀጣይ ግንቦት በሚደረገው ምርጫ ለማሸነፍ የተወሰኑ ሀገራትን ለማሳመን ጥረት መጀመራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ ይሁንና ራይላ ኦዲንጋ…
Read More
የአፍሪካ ህብረት ሳይጋበዙ ጉባኤውን ለመሳተፍ የሚመጡ ሰዎችን አስጠነቀቀ

የአፍሪካ ህብረት ሳይጋበዙ ጉባኤውን ለመሳተፍ የሚመጡ ሰዎችን አስጠነቀቀ

የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች የሚሳተፉበት 44ኛው የአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ነው። የህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ደግሞ የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ የሚካሄድ ሲሆን በዚህ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ለሚመጡ ታዛቢ ሀገራት ማስጠንቀቂያ አውጥቷል፡፡ ህብረቱ ባወጣው መግለጫ በታዛቢነት እንዲሳተፉ ከተጋበዙ ሀገራት እና ተቋማት ውጪ የሚመጡ ተሳታፊዎችን እንደማያስተናግድ አስጠንቅቋል፡፡ 37ኛው የህብረቱ መሪዎች እና 44ኛው የህብረቱ ስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ጉባኤን በታዛቢነት እንዲሳተፉ ከተፈቀደላቸው ሀገራት እና ተቋማት ውጪ እንዳይመጡ እና ፈቃድ የተሰጣቸው ደግሞ ከአንድ ተወካይ በላይ እንዳይመጡ ሲልም ህብረቱ አሳስቧል፡፡ ከዚህ በፊት በአፍሪካ ህብረት ጉባኤዎች ላይ በታዛቢነት እንዲሳተፉ ፈቃድ የተሰጣቸው ሀገራት እና ተቋማትም ፈቃዳቸውን እንዲያድሱ ሲልም…
Read More