30
Jun
በፈረንጆች 2022 ብቻ በኢትዮጵያ በረሃብና በበሽታ ከ200 ሺሕ በላይ ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ በፈረንጆቹ 2022 ዓመት ብቻ በኢትዮጵያ በረሃብ እና ከረሀብ ጋር ተያይዘው ከሚከሰቱ በሽታዎች በተያያዘ ከ200 ሺሕ በላይ ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉ ተገልጿል። በዚህም በኢትዮጵያ በረሃብና ተያያዥ በሽታዎች የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በየዓመቱ እየጨመረ መምጣቱ የተጠቀሰ ሲሆን፤ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ለእርዳታ የሚልኩት እህል ለግል ጥቅም ሲውል እና በገበያ ላይ ሲሸጥ አረጋግጠናል በሚል የሰብዓዊ እርዳታ መቋረጡም፣ በዚህ ወቅት በረሃብ እና በበሽታ ለሞቱ ሰዎች እንደ ዋና ምክንያት ተጠቅሷል። እንዲሁም በዚያው ዓመት በተፈጠሩ ግጭቶች የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ከ100 ሺሕ በላይ መሆኑን ግሎባል ፒስ ኢንዴክስ በድኅረ ገጹ አስነብቧል፡፡ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገራት የእርስ በርስ ግጭት…