27
Mar
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የኦዲት ግኝት ሪፖርት ላይ መክሯል፡፡ የቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር እና የዩንቨርሲቲው አመራር አባላት በጋራ ባደረጉት ውይይት ላይ እንደተገለጸው ለሶስተኛ ድግሪ በሚል ለትምህርት የተላኩ እና የጠፉ የዩንቨርሲቲው መምህራን ጉዳይ ዋነኛው ነው፡፡ የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ እና የፌደራል ዋና ኦዲተር አመራሮች ዩንቨርሲቲው ለሶስተኛ ድግሪ ትምህርት ብሎ ስፖንሰር ሆኖ የላካቸው መምህራን በወቅቱ ትምህርታቸውን አጠናቀው እንዳልተመለሱ፣ ዩንቨርሲቲውም ለነዚህ መምህራን የከፈለውን ከ7 ሚሊዮን በላይ ብር ገንዘብ ለምን ተመላሽ አላደረክም? በሚል ጥያቄ አንስተዋል፡፡ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ደረጀ እንግዳ (ዶ/ር) ከ2011 ዓ.ም…