UNDP

ኢትዮጵያ ለምርጫ ስርዓት ማጠናከሪያ የ30 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አገኘች

ኢትዮጵያ ለምርጫ ስርዓት ማጠናከሪያ የ30 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አገኘች

ኢትዮጵያ ዘላቂ ዲሞክራሲን ለማስፈን የሚያስችላትን የምርጫ ስርአት እንድታጠናክር ለማግዝ የሚውል የ30 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር የፋናንስ ድጋፍ ስምምነት ፈርማለች፡፡ ስምምነቱን የኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒስቴር፣ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና የተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት መካካል ተፈርሟል፡፡ የበጀት ድጋፉ የምርጫ ቦርድ ተቋማዊ መዋቅርን ለማጠናከር ነፃ፣ ፍትሃዊ፣ አሳታፊ ፣ተአማኒና ደረጃውን የጠበቀ ምርጫና ህዝበ ውሳኔ እንዲያካሂድ ተቋሙን ማጠናከር፣ ከሲቪክ ተቋማት በጋራ በመሆን በምርጫ ሂደት የሴቶችና ወጣቶች ተሳትፎን ለማሳደግ ይውላል ተብሏል፡፡ እንዲሁም የበጀት ድጋፉ በኢትዮጵያ ነፃ ፍትሀዊ እና ተአማኒ ምርጫ እንዲያከሂድ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር እንደሚውልም የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ይህ የበጀት ድጋፍ ፕሮጀክት በሚቀጥሉት አራት አመታት ውስጥ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን የሀገሪቱን የምርጫ ስርአት በማጠናከር ዘላቂ ዴሞክራሲን ለማስፈን አስተዋጽኦ…
Read More