05
Apr
ኢትዮጵያ እና ዓለም ባንክ የ1 ነጥብ 72 ቢሊዮን ዶላር ወይም የ97 ቢሊዮን ብር እርዳታ እና በድር ስምምነት መፈራረማቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ የገንዘብ ድጋፍ ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ እና በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ ተወካይ የሆኑት ኦስማን ዲዮን ተፈራርመዋል ተብሏል፡፡ ከዓለም ባንክ ከተገኘው የገንዘብ ድጋፍ ውስጥ 850 ሚሊዮን ዶላር ያህሉ በእርዳታ ለኢትዮጵያ የተለያዩ ስራዎችን ለመደገፍ እንደሚውል ተገልጿል፡፡ ቀሪው ገንዘብ ደግሞ ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን ለማስፋፋት እና ለማከናወን በሚል በብድር መልኩ ከባንኩ እንደተሰጠ ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡ በእርዳታ ከተሰጠው ገንዘብ ውስጥ 500 ሚሊዮን ዶላሩ ለገጠር አካባቢዎች የምግብ ዋስትና፣ የአየር ንብረት ለውጥ ስራዎችን ለመደገፍ፣ 82 ዶላሩ ደግሞ በከተማ አካባቢዎች ምግብ ዋስትና ስራዎችን ለማረጋገጥ…