Port

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ እንደሚሰጋት ገለጸች

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ እንደሚሰጋት ገለጸች

የአሜሪካ የታችኛው ምክር ቤት ኮንግረስ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ የአፍሪካ ጉዳዮች ንኡስ ኮሚቴ፣  ‘”በኢትዮጵያ ተስፋ ወይንስ ስጋት፣ የአሜሪካ ፖሊሲ ሁኔታ’’ ላይ ትላንት ምሸት ምስክርነት ሰምቷል፡፡ የኮሚቴው አባላት ለአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር፣ ስለ ባህር በር በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ስለተነሳው ጥያቄ የአሜሪካን አቋም ጠይቀዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ “የወደብ ጉዳይ ለኢትዮጵያ የህልውና ጉዳይ ነው” ብለው መናገራቸው በቀጠናው ካሉ አገራት አልፎ ለአሜሪካ ስጋት እንደሆነ ማይክ ሐመር ተናግረዋል። ይሁን እንጂ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የባህር በር ፍላጎት በኃይል ተፈጻሚ እንደማይሆን በይፋ እንዲሁም በግል ማረጋገጫ እንደሰጧቸው አመልክተዋል። ጥያቄው በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ስጋት እንደፈጠረ የጠቆሙት ማይክ ሐመር፣ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ የሚቀጠል ከሆነ…
Read More
የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ስለባህር በር አስተያየት ሲሰጡ እንዲጠነቀቁ ተጠየቀ

የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ስለባህር በር አስተያየት ሲሰጡ እንዲጠነቀቁ ተጠየቀ

ባለስልጣናት ስለ ባህር በር ጉዳይ የሚሰጡት መግለጫ የተጠናና ጥንቃቄ የተሞላበት መሆን እንዳለበት ምሁራን አሳስበዋል፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ የባህር በር ዙሪያ የምሁራን ውይይት መድረክ አዘጋጅቶ ነበር፡፡ በዚህ የምሁራን መድረክ ላይ ጥናት ያቀረቡና ውይይት ያደረጉ ምሁራን፣ መንግሥት ስለባህር በር የሚሰጣቸው መረጃዎች የጎረቤት አገሮችን የማያሠጉና ጥንቃቄ የተሞላባቸው እንዲሆኑ አሳስበዋል፡፡ ‹‹ፍትሐዊ የወደብ አጠቃቀም ለአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ሰላምና ልማት›› በሚል ርዕስ በተስተናገደው በዚህ ዓውደ ጥናት ላይ፣ ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ የባህር በር ባለቤት መሆን ስለምትችልባቸው አማራጮች ሰፊ ምሁራዊ ውይይት ተካሂዷል፡፡ በጥናት መድረኩ ላይ ለኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄን በማስመለስ ታሪካዊ ድል ያስመዘገቡ ያለፈው ትውልድ ምርጥ ተሞክሮ ታሪካዊ ድል እንደነበር ተገልጿል፡፡ በሰላማዊ መንገድ ኤርትራን በፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ ጋር…
Read More
ኢትዮጵያ ያቀረበችው የባህር በር ጥያቄ በጎረቤት ሀገራት ውድቅ ተደረገ

ኢትዮጵያ ያቀረበችው የባህር በር ጥያቄ በጎረቤት ሀገራት ውድቅ ተደረገ

ከሰሞኑ ጠቅላይ ሚኒስት አብይ አህመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ የህዝቧን የመልማት ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት የባህር በር ያስፈልጋታል ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል፡፡ ኢትዮጵያ የጣላቁ ህዳሴ ግድብን ስትገነባ ጉዳዩ ያሳሰባቸው ሀገራት ጠይቀዋል፣ እኛም የባህር በር እንዲኖረን መጠየቅ አለብን ሲሉም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የባህር በር ያስፈልጋታል ያበሉ እንጂ ስለየትኛው የባህር በር ግን ስም አልጠቀሱም ነበር፡፡ ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ ጎረቤት የሆኑት እና የባህር በር ያላቸው ኤርትራ፣ ጅቡቲ እና ሶማሊያ ሲሆኑ ሶስቱም ሀገራት የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ ውድቅ አድርገዋል፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ አስቀድሞ መግለጫ ያወጣው የኤርትራ መንግስት ሲሆን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ በኩል ባወጣው መግለጫ ሀገሪቱ ሀብቷን ለማንም አሳልፋ እንደማትሰጥ፣ እስካሁንም የተጀመረ ምንም…
Read More
ኢትዮጵያ የሲንጋፖር ኩባንያን ወደ ሀገሯ እንዲመጣ ጋበዘች

ኢትዮጵያ የሲንጋፖር ኩባንያን ወደ ሀገሯ እንዲመጣ ጋበዘች

የሲንጋፖር የወደብ ባለስልጣን በኢትዮጵያ በሎጀስቲክስ ኢንቨስትመንት እንዲሰማራ ጥሪ ቀረበ ዓለም አቀፍ የእስያ ኩባንያዎችን ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ እና ኢንቨስት እንዲያደርጉ ለማሳመን የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ሲንጋፖርን በመጎብኘት ላይ ናቸው፡፡ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ጋር በመሆን ሲንጋፖር የሚገኘውን የሲንጋፖር የወደብ ባለስልጣን ጎብኝተዋል። ሁለቱ የኢንቨስትመንት አመራሮች ከሲንጋፖር ወደብ ባለስልጣን ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል። በውይይቱም የሲንጋፖር የወደብ ባለስልጣን በኢትዮጵያ በሎጀስቲክስ ኢንቨስትመንት እንዲሰማራ ጠይቀዋል። የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ፣ ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላትን ከፍተኛ ፍላጎት ገልፀው ባለስልጣኑ በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት የሚሰማራበትንና ልምድ የሚያካፍልበት መንገድ እንዲኖር ጥሪ አቅርበዋል። የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ በበኩላቸው ፈጣን…
Read More