26
Feb
ኢትዮጵያ እና ግብጽን ጨምሮ አምስት ሀገራት 12 ሺህ ገደማ ወታደሮችን ለማሰማራት ተስማምተዋል የአፍሪካ ህብረት እና የሶማሊያ መንግስት በተልዕኮው በሚሳተፉ ሀገራት ዝርዝር እንዲሁም በሚያዋጡት የወታደር ቁጥር ዙሪያ ከስምምነት ደርሰዋል በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የድጋፍ ተልዕኮ (አውሶም) ውስጥ በሚሳተፉ ሀገራት እና በሚያዋጡት የወታደር ቁጥር ዙሪያ ስምምነት ላይ ተደርሷል ተብሏል። የሶማሊያ ፌዴራል መንግስት እና የአፍሪካ ህብረት በአዲሱ የአፍሪካ ህብረት ተልዕኮ ላይ በመወከል ወታደር በሚያዋጡ ሀገራት ቁጥር ላይ መስማማታቸውን ቪኦኤ ዘግቧል። አትዮጵያ እና ሶማሊያ የኢትዮጵያ ጦር በአዲሱ የአፍሪካ ህብረት ሰላም ማስከበር ተልዕኮ እንዲሳተፍ ተስማሙ የሞቃዲሾ መንግስት ከብሩንዲ እና ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ገብቶበት የነበረውን ውዝግብ ተከትሎ የተሳታፊ ሀገራትን ቁጥር እና የሚልኳቸውን ወታደሮች መጠን ለመወሰን…