Turkey

ኢትዮጵያ በቱርኩ ያፒ መርከዚ የባቡር ግንባታ ኩባንያ ላይ ክስ መሰረተች

ኢትዮጵያ በቱርኩ ያፒ መርከዚ የባቡር ግንባታ ኩባንያ ላይ ክስ መሰረተች

የቱርኩ ያፒ መርከዚ ኩባንያ በኢትዮጵያ የጀመረውን የባቡር መስመር ግንባታ ሳያጠናቅቅ ከሀገር ወጥቷል ተብሏል፡፡ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣ የቱርኩ ተቋራጭ ያፒ መርከዚ ኩባንያ የአዋሽ-ወልድያ-መቀሌ የባቡር ሐዲድ ግንባታን ሳያጠናቅቅ በመውጣቱ 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ካሳ እንዲከፍለው ክስ መመስረቱ ተገልጿል፡፡ ያፒ መርከዚ የተሰኘው የቱርክ ስራ ተቋራጭ ኩባንያ በ2007 ዓ.ም 392 ኪሎ ሜትር የሚረዝም የባቡር መስመር ግንባታ በማካሄድ ላይ ነበር፡፡ ይህ የባቡር መስመር የመካከለኛ እና ሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች ከጅቡቲ ወደብ ጋር የተሳለጠ የትራንስፖርት እንቅስቀሴ እንዲኖራቸው ታስቦ በመገንባት ላይ ነበር፡፡ ከቱርኩ ኤግዚም ባንክ በተገኘ 1 ነትብ 9 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ግንባታው እየተካሄደ የነበረው ይህ የባቡር መስመር ሊጠናቀቅ ጥቂት መሰረተ ልማቶች ሲቀሩት በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት…
Read More
ኢትዮጵያ የበርበራ ወደብን መጠቀም ጀመረች

ኢትዮጵያ የበርበራ ወደብን መጠቀም ጀመረች

የሶማሌላንድ የገንዘብ እና ልማት ሚኒስቴር ዛሬ በሶማሌላንድ በርበራ ወደብ የኢትዮጵያ ትራንዚት ማሳለጫ ቢሮዎች ስራ መጀመራቸውን ገልጿል። የሶማሌላንድ የንግድና ቱሪዝም ሚኒስቴር ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አብዲረሺድ ኢብራሂም ደግሞ  "የሶማሌላንድ መንግሥት በበርበራ ወደብ የኢትዮጵያ ትራንዚት ማሳለጫ ቢሮዎችን ስራ አስጀምሯል " ሲል ይፋ አድርገዋል። "ይህ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ትልቅ ምዕራፍ ነው" ሲሉ ገልጸዋል። ይህ ውጥን ቀጠናዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስርን ለማጠናከር ሶማሌላንድ ያላትን ቁርጠኝነት ያሳያል ሲሉ አክለዋል። ቢሮው በወደቡ የሚራገፉ ጭነቶችን ወደ ኢትዮጵያ የተለያዩ መዳረሻዎች እንዲጓጓዙ የሚያሳልጥ ነውም ተብሏል። በርበራ ወደብ በተባበሩት አረብ ኤሜሬትሱ DP World ይተዳደራል የተባለ ሲሆን የበርበራ ወብ ዋና ስራ አስፈፃሚ ስፓቺ ዋታንቫራቺ ተገኝተው…
Read More
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ሁለተኛውን ዙር ድርድር በአንካራ ጀመሩ

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ሁለተኛውን ዙር ድርድር በአንካራ ጀመሩ

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ከወደብ ጋር በተያያዘ በመካከላቸው የተፈጠረዉን ዉጥረት ለመፍታት ሁለተኛ ዙር ድርድራቸውን በአንካራ ጀምረዋል፡፡ የቱርክ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይፕ ኤርዶሃን በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ንትርክ ዙሪያ ከፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ጋር በስልክ መምከራቸውም ተሰምቷል፡፡ የቱርክ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይፕ ኤርዶሃን ከሶማሊያ አቻቸዉ ሀሰን ሼክ ማህሙድ ጋር በስልክ መምከራቸዉ ተዘግቧል። በቱርክ እና በሶማሊያ መካከል ያለውን ትብብር አስፈላጊነት በማጉላት አንካራ ፥ በሞቃዲሾ እና በአዲስ አበባ መካከል ያለውን አለመግባባት ለመፍታት ጥረቷን እንደምትቀጥል የቱርክ ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በኤክስ ገጹ ላይ ጽፏል። በዛሬዉ እለት በቱርኪዬ ርዕሰ መዲና አንካራ ከሚካሄደው ሁለተኛ ዙር የሶማሊያ እና የኢትዮጵያ ድርድር ውጥረቱን ለማርገብ ተጨባጭ ውጤት ይጠበቃል ብሏል። መሪዎቹ በስልክ ዉይይታቸዊ በሁለትዮሽ ግንኙነት እንዲሁም በአህጉራዊ እና…
Read More
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ከወደብ ስምምነት ውጪ በሌሎች ጉዳዮችም እየተደራደሩ መሆኑን ገለጹ

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ከወደብ ስምምነት ውጪ በሌሎች ጉዳዮችም እየተደራደሩ መሆኑን ገለጹ

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ በወቅታዊ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል። ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው ላይ ካነሷቸው ጉዳዮች መካከል የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ጉዳይ ዋነኛው ነው። በቱርክ አደራዳሪነት በአንካራ የተጀመረው የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ድርድር ሁለተኛው ዙር የፊታችን ነሀሴ 27 ቀን 2016 ዓ.ም ይቀጥላል የተባለ ሲሆን ይህ ድርድር ምን ያህል ከውጭ ጣልቃ ገብነት የተጠበቀ ነው?  የሚል ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ተከታዩን ብለዋል። "ኢትዮጵያ በታሪኳ ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ ስትደራደር ቆይታለች፣ አንድም ጊዜ በውጭ ጣልቃ ገብነቶች ጥቅሟን አሳልፋ ሰጥታ አታውቅም" ብለዋል። "በአንካራ እየተካሄደ ያለው የሁለትዮሽ ድርድርም ብሔራዊ ጥቅማችንን ባስጠበቀ መንገድ ይቀጥላል" ያሉት አምባሳደር ነብዩ በድርድሩ ላይ ምንም አይነት ጣልቃ ገብነት እንደሌለ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ…
Read More
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በአንካራ ድርድር ጀመሩ

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በአንካራ ድርድር ጀመሩ

ቱርክ ግንኙነታቸው የሻከረውን ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ማደራደር መጀመሯ ተገልጿል። ሬውተርስ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮቹን ጠቅሶ እንዳስነበበው ድርድሩ በቱርክ መዲና አንካራ በመካሄድ ለይ ይገኛል። ይሁን እንጂ አደራዳሪዋ ቱርክም ሆነች ተደራዳሪዎቹ እስካሁን ማረጋገጫ አልሰጡም። የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አህመድ ሙአሊም ፊቂ የመሩት ልኡክ በትናንትናው እለት ወደ ቱርክ ማቅናቱን ቢዘግቡም የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማረጋገጫ አልሰጠም። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣንም በአንካራ ተጀምሯል ስለተባለው ድርድር ምንም መናገር አንፈልግም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። የሶማሊላንድ መንግስት ቃል አቀባይ በበኩላቸው በድርድሩ ላይ እየተሳተፉ እንዳልሆነ ለሬውተርስ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በጥር ወር ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ጋር በደረሰችው የወደብ ስምምነት ምክንያት የአዲስ አበባ እና ሞቃዲሾ ግንኙነት መሻከሩ ይታወቃል።…
Read More
ሶማሊያ እና ቱርክ የጋዝ እና ነዳጅ ልማት ሰምምነት ተፈራረመሙ

ሶማሊያ እና ቱርክ የጋዝ እና ነዳጅ ልማት ሰምምነት ተፈራረመሙ

 ቱርክ ከሶማሊያ ጋር በውቅያኖስ ውስጥ ጋዝ እና ነዳጅ ለማልማት በትናንትናው እለት ስምምነት ማድረጓን የቱርክ የኢነርጂ ሚኒስትር ተናግረዋል። ይህ ስምምነት ሁለቱ ሀገራት ባለፈው ወር ከተፈራረሙት ወታደራዊ ስምምነት የቀጠለ እና የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን የበለጠ የሚያጠናክር ነው ተብሏል። ስምምነቱ በሁለቱ መንግስታት መካከል የተፈረመ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ በሶማሊያ መሬት እና ውሃማ አካላት ውስጥ ነዳጅ መፈለግን እና ማምረትን የሚያካትት መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል። በስምምነቱ መሰረት የሶማሊያ ሀብት ለሶማሊያውያን ለማዋል እና በአፍሪካ ቀንድ የቱርክን ተጽዕኖ ከፍ ለማድረግ አላማ እንዳላቸው ሚኒስትሩ አልፓርስላን ባይራክታር ገልጸዋል። በሌላ በኩል የሶማሊያ ድንበር በሙሉ ለቱርክ መሸጡ ያስቆጣቸው ሶማሊያዊያን በሞቃዲሾ የተቃውሞ ሰልፍ መውጣታቸውን የሶማሊያ የዜና ምንጮች ዘግበዋል። ኢትዮጵያ እና ራስ ገዟ ሶማሊላንድ ከሁለት ወር በፊት…
Read More
ማንችስተር ሲቲ እና ኢንተርሚላን ለአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ አለፉ

ማንችስተር ሲቲ እና ኢንተርሚላን ለአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ አለፉ

በአውሮፓ ምርጥ እግር ኳስ ክለቦች ሙካከል ሲካሄድ የቆየው የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ ተፋላሚዎች ታውቀዋል። ትናንት ምሽት በእንግሊዝ ማንችስተር ከተማ በሪያል ማድሪድ እና ማንችስተር ሲቲ መካከል የተካሄደው ውድድር በሲቲ የበላይነት ተጠናቋል። በርናርዶ ሲልቫ ሁለት ጎል፣ አልቫሬዝ እና ሚሊታኦ በራሱ ግብ ላይ ባስቆጠሯቸው ጎሎች ሲቲ በቱርክ ኢስታምቡል ከተማ ለሚካሄደው የፍጻሜ ውድድር ማለፍ ችሏል። የጣልያኑ ኢንተር ሚላን በፍጻሜው ማንችስተር ሲቲን የሚገጥም ሲሆን ጨዋታው ሰኔ 3 ቀን 2015 ዓ.ም ምሽት 4:00 ላይ ይካሄዳል ተብሏል። የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ውድድርን የስፔኑ ሪያል ማድሪድ 14 ጊዜ በማሸነፍ ቀድሚው ክለብ ሆኖ ተመዝግቧል። የፍጻሜ ተፋላሚው ማንችስተር ሲቲ እስካሁን አንድም ጊዜ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግን ያላሸነፈ ሲሆን ሌላኛው የፍጻሜ ተፋላሚ ኢንተርሚላን ሶስት…
Read More