12
Dec
ከአንድ ዓመት በፊት ኢትዮጵያ ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ጋር የወደብ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡ ስምምነቱን ተከትሎ ሶማሊያ ሉዓላዊነቴን የሚጥስ ነው በሚል ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት አቋርጣም ነበር፡፡ የሁለቱም ሀገራት ወዳጅ የሆነችው ቱርክ በአንካራ የውይይት መድረክ ያዘጋጀች ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ በትናንትናው ዕለት ወደ አንካራ አቅንተው ነበር፡፡ የቱርክ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን የሁለቱን ሀገራት መሪዎች በተናጠል አግኝተው እንዳወያዩ አናዶሉ ዘግቧል፡፡ ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ኢትዮጵያ እና ሱማልያ ሀለቱንም ሀገራት በሚያግባባ መልኩ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተናግረዋል። ኤርዶጋን ሁለቱ ሀገራት በጋራ ይፋ የሚያደርጉት የስምምነት ዶክመንት እንደተዘጋጀ ጠቅሰው ዶክመንቱ ሀገራቱ የበፊቱን ሳይሆን መጪውን ግዜ እንዴት በጋራ አብረው ተከባብረው እና በመልካም ጉርብትና እንደሚወጡት…