Somalia

የኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ ስምምነት በምስራቅ አፍሪካ አዲስ የዲፕሎማሲ ፍትጊያ መፍጠሩ ተገለጸ

የኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ ስምምነት በምስራቅ አፍሪካ አዲስ የዲፕሎማሲ ፍትጊያ መፍጠሩ ተገለጸ

በቀይ ባህር ላይ ወደብ እንደሚያስፈልጋት ስትገልጽ የቆየችው ኢትዮጵያ ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ወደብ በሊዝ መግዛቷን ማስታወቋ ይታወሳል፡፡ የሁለቱ አካላት የመግባቢያ ስምምነት ኢትዮጵያ በበርበራ ወደብ 20 ኪሎ ሜትር ላይ ወደብ እና ወታደራዊ ቤዝ እንዲኖራት የሚፈቅድ ሲሆን በአንጻሩ ደግሞ ኢትዮጵያ ለሶማሊላንድ የሀገርነት እውቅና እንድትሰጥ ይጠቅሳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ የ20 በመቶ ድርሻ እንዲኖራት ይደረጋል የተባለ ሲሆን በአንድ ወር ውስጥ ተጨማሪ ድርድሮች እንደሚካሄዱ ተገልጿል፡፡ ይህን ተከትሎም ሶማሊያ የኢትዮጵያን እና የግዛቴ አካል ናት የምትላት ሶማሊላንድ ያደረጉት ስምምነት ሉዓላዊነቴን የሚጥስ ዓለም አቀፍ ህግንም የሚጥስ እንደሆነ አስታውቃለች፡፡ ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ ያደረጉት ስምምነት ሶማሊያ አልሻባብን ለማጥፋት የጀመረችውን ዘመቻ እንደሚያስተጓጉል እና የሽብር ቡድኑ ዳግም እንዲያንሰራራ እንደሚያደርግም…
Read More
ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ወደብ በሊዝ መግዛቷን ገለጸች

ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ወደብ በሊዝ መግዛቷን ገለጸች

በቀይ ባህር ላይ ወደብ እንደሚያስፈልጋት ስትገልጽ የቆየችው ኢትዮጵያ ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ወደብ በሊዝ መግዛቷን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡ እንደ ጽህፈት ቤቱ መግለጫ ከሆነ የባህር በር የምታገኝበትን የመግባቢያ ስምምነት ከሶማሌ ላንድ ጋር ተፈራርማለች፡፡ የባህር በር ሊዝ ስምምነቱን ጠቅላይ ሚኒስትር  ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማሌ ላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ እንደተፈራረሙ ተገልጿል። የኢትዮጵያ እና ራስ ገዟ ሶማሊላንድ ስምምነት ኢትዮጵያ የቀይ ባህር በር እንዲኖራት ለያዘችው ጥረት ጥሩ መደላደል ሊፈጥር ይችላልም ተብሏል፡፡ ይሁንና የባህር በር ሊዝ ስምምነቱ ለምን ያህል ጊዜ፣ በምን ያህል ገንዘብ እና የስምምነቱ ዝርዝር መረጃ እስካሁን በማንኛውም ወገን ይፋ አልተደረገም፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ከወራት በፊት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት…
Read More
የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ስለባህር በር አስተያየት ሲሰጡ እንዲጠነቀቁ ተጠየቀ

የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ስለባህር በር አስተያየት ሲሰጡ እንዲጠነቀቁ ተጠየቀ

ባለስልጣናት ስለ ባህር በር ጉዳይ የሚሰጡት መግለጫ የተጠናና ጥንቃቄ የተሞላበት መሆን እንዳለበት ምሁራን አሳስበዋል፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ የባህር በር ዙሪያ የምሁራን ውይይት መድረክ አዘጋጅቶ ነበር፡፡ በዚህ የምሁራን መድረክ ላይ ጥናት ያቀረቡና ውይይት ያደረጉ ምሁራን፣ መንግሥት ስለባህር በር የሚሰጣቸው መረጃዎች የጎረቤት አገሮችን የማያሠጉና ጥንቃቄ የተሞላባቸው እንዲሆኑ አሳስበዋል፡፡ ‹‹ፍትሐዊ የወደብ አጠቃቀም ለአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ሰላምና ልማት›› በሚል ርዕስ በተስተናገደው በዚህ ዓውደ ጥናት ላይ፣ ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ የባህር በር ባለቤት መሆን ስለምትችልባቸው አማራጮች ሰፊ ምሁራዊ ውይይት ተካሂዷል፡፡ በጥናት መድረኩ ላይ ለኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄን በማስመለስ ታሪካዊ ድል ያስመዘገቡ ያለፈው ትውልድ ምርጥ ተሞክሮ ታሪካዊ ድል እንደነበር ተገልጿል፡፡ በሰላማዊ መንገድ ኤርትራን በፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ ጋር…
Read More
ኢትዮጵያ ያቀረበችው የባህር በር ጥያቄ በጎረቤት ሀገራት ውድቅ ተደረገ

ኢትዮጵያ ያቀረበችው የባህር በር ጥያቄ በጎረቤት ሀገራት ውድቅ ተደረገ

ከሰሞኑ ጠቅላይ ሚኒስት አብይ አህመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ የህዝቧን የመልማት ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት የባህር በር ያስፈልጋታል ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል፡፡ ኢትዮጵያ የጣላቁ ህዳሴ ግድብን ስትገነባ ጉዳዩ ያሳሰባቸው ሀገራት ጠይቀዋል፣ እኛም የባህር በር እንዲኖረን መጠየቅ አለብን ሲሉም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የባህር በር ያስፈልጋታል ያበሉ እንጂ ስለየትኛው የባህር በር ግን ስም አልጠቀሱም ነበር፡፡ ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ ጎረቤት የሆኑት እና የባህር በር ያላቸው ኤርትራ፣ ጅቡቲ እና ሶማሊያ ሲሆኑ ሶስቱም ሀገራት የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ ውድቅ አድርገዋል፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ አስቀድሞ መግለጫ ያወጣው የኤርትራ መንግስት ሲሆን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ በኩል ባወጣው መግለጫ ሀገሪቱ ሀብቷን ለማንም አሳልፋ እንደማትሰጥ፣ እስካሁንም የተጀመረ ምንም…
Read More
ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ የቀረበባትን ክስ ውድቅ አደረገች

ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ የቀረበባትን ክስ ውድቅ አደረገች

ሶማሊላንድ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ልዩ ኃይሎች ድንበር አልፈው በሶሎ ግዛት ላስአኖድ ከተማ ጦርነት ውስጥ እየተሳተፉ ነው ስትል ክስ አቅርባ ነበር። በፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ የሚመራው የሶማሌላንድ ካቢኔ ባወጣው መግለጫ ግጭት ባለባት ላስአኖድ ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ኃይሎች በተጨማሪ የሶማሊያ እና የፑንትላንድ ወታደሮች ይገኛሉ ብሏል፡፡ ካቢኔው የሶማሌ ላንድን ዓለም አቀፋዊ ድንበር አልፈው ገብተዋል ያላቸው እነዚህ ኃይሎች ከአካባቢው እንዲወጡም አሳስቧል።  ለሶማሊላንድ ክስ ምላሽ የሰጠው የሶማሌ ክልል መንግስት በላሳኖድ ከተማ በሚካሄደው ጦርነት አንድም የሶማሌ ክልል ኃይል አባል የለም ያለ ሲሆን፣ መግለጫውንም ኃላፊነት የጎደለው ውንጀላ እንደሆነ ገልጿል፡፡ በጉዳዩ ላይ የተናገሩት የሶማሌ ክልል መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ዐብዱልቃድር ረሺድ ‹‹እኛ የሌላ ሀገር ፖለቲካ ውስጥ እጅ…
Read More