Somali

ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ የቀረበባትን ክስ ውድቅ አደረገች

ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ የቀረበባትን ክስ ውድቅ አደረገች

ሶማሊላንድ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ልዩ ኃይሎች ድንበር አልፈው በሶሎ ግዛት ላስአኖድ ከተማ ጦርነት ውስጥ እየተሳተፉ ነው ስትል ክስ አቅርባ ነበር። በፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ የሚመራው የሶማሌላንድ ካቢኔ ባወጣው መግለጫ ግጭት ባለባት ላስአኖድ ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ኃይሎች በተጨማሪ የሶማሊያ እና የፑንትላንድ ወታደሮች ይገኛሉ ብሏል፡፡ ካቢኔው የሶማሌ ላንድን ዓለም አቀፋዊ ድንበር አልፈው ገብተዋል ያላቸው እነዚህ ኃይሎች ከአካባቢው እንዲወጡም አሳስቧል።  ለሶማሊላንድ ክስ ምላሽ የሰጠው የሶማሌ ክልል መንግስት በላሳኖድ ከተማ በሚካሄደው ጦርነት አንድም የሶማሌ ክልል ኃይል አባል የለም ያለ ሲሆን፣ መግለጫውንም ኃላፊነት የጎደለው ውንጀላ እንደሆነ ገልጿል፡፡ በጉዳዩ ላይ የተናገሩት የሶማሌ ክልል መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ዐብዱልቃድር ረሺድ ‹‹እኛ የሌላ ሀገር ፖለቲካ ውስጥ እጅ…
Read More