04
Feb
የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፎልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እንዳሉት ሰራዊቱ “ከየትኛውም አቅጣጫ የሚሰነዘርበትን ጥቃት” ለመመከት ዝግጁ ነው ብለዋል፡፡ ዋና አዛዡ የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ በሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ለ24ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን መኮንኖች ባስመረቀበት ወቅት እንዳሉት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ወቅት “በሰላማዊ መንገድ የባህር በር ለማግኘት ጥረት እያደረገች ያለችበት ነው” ያሉት አዛዡ የሀገሪቱ ታሪካዊ ጠላቶች የውስጥ ችግሮችን ለማባባስ “የቋመጡበት እና የቆረጡበት” ወቅት እንደሆነም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ “ከቀይ ባህር ተገፍታ በመቆየቷ የደረሰባትን የኢኮኖሚና የጸጥታ ተግዳሮቶችን እና ስብራቶችን” ለመቅረፍ “እየሞከረች” ያለችበት መሆኑን ልብ ሊሉት እንደሚገባ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ ለተመራቂ ወታደራዊ መኮንኖቹ አሳስበዋል። ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ…