16
Apr
የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳድር መንግስት ወጪ ቅነሳ ላይ ሲሆን አሁን ደግሞ ኢምባሲዎችን ለመዝጋት ማሰባቸው ተገልጿል፡፡ ፖለቲኮ እንደዘገበው ከሆነ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የወጪ ቅነሳ አዲስ እቅድ አውጥቷል፡፡ በዚህ እቅድ መሰረትም የመስሪያ ቤቱን አመታዊ ወጪ በግማሽ በመቶ ለመቀነስ መታሰቡ ተገልጿል፡፡ እቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ ከቀረቡ ምክረ ሀሳቦች መካከል በዓለም ላይ ያሉ የአሜሪካ ኢምባሲዎች እና ቆንሱላ ጽህፈት ቤቶችን ለመዝጋት ታቅዷል ተብሏል፡፡ በዓለማችን ቁጥር አንድ ባለጸጋ ኢለን መስክ ምክር የሚመራው የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳድር መንግስት አሁን ደግሞ ትኩረቱን ወደ ኢምባሲዎች መዝጋት አዙሯል፡፡ ከቀረቡት ምክረ ሀሳቦች ውስጥ 10 የአሜሪካ ኤምባሲዎች እና 17 ቆንስላ ጽህፈት ቤቶችን ለመዝጋት መታቀዱ ተገልጿል፡፡ በእቅድ ደረጃ እንዲዘጉ ከተባሉት ኤምባሲዎች እና…