11
Dec
የሶማሌላንድ የገንዘብ እና ልማት ሚኒስቴር ዛሬ በሶማሌላንድ በርበራ ወደብ የኢትዮጵያ ትራንዚት ማሳለጫ ቢሮዎች ስራ መጀመራቸውን ገልጿል። የሶማሌላንድ የንግድና ቱሪዝም ሚኒስቴር ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አብዲረሺድ ኢብራሂም ደግሞ "የሶማሌላንድ መንግሥት በበርበራ ወደብ የኢትዮጵያ ትራንዚት ማሳለጫ ቢሮዎችን ስራ አስጀምሯል " ሲል ይፋ አድርገዋል። "ይህ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ትልቅ ምዕራፍ ነው" ሲሉ ገልጸዋል። ይህ ውጥን ቀጠናዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስርን ለማጠናከር ሶማሌላንድ ያላትን ቁርጠኝነት ያሳያል ሲሉ አክለዋል። ቢሮው በወደቡ የሚራገፉ ጭነቶችን ወደ ኢትዮጵያ የተለያዩ መዳረሻዎች እንዲጓጓዙ የሚያሳልጥ ነውም ተብሏል። በርበራ ወደብ በተባበሩት አረብ ኤሜሬትሱ DP World ይተዳደራል የተባለ ሲሆን የበርበራ ወብ ዋና ስራ አስፈፃሚ ስፓቺ ዋታንቫራቺ ተገኝተው…