24
Feb
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የኢትዮጵያ ጦር በአዲሱ የአፍሪካ ህብረት ሰላም ማስከበር ተልዕኮ እንዲሳተፍ ተስማሙ፡፡ በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የድጋፍ ተልዕኮ (አውሶም) ውስጥ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እንዲሰማራ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መስማማታቸው ተገልጿ፡፡ ከሁለት ቀናት በፊት ወደ ሶማሊያ ያቀኑት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ከሶማሊያ መከላከያ ሰራዊት አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ኦዳዋ ዩሱፍ ራጌ ጋር ተገናኝተው በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡ ስምምነቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሃሙድ በቅርቡ በአዲስ አበባ ያደረጉትን የሁለትዮሽ ውይይት ተከትሎ የተደረገ የቴክኒክ ምክክር አካል ነው ተብሏል፡፡ የጦር መሪዎቹ የሞቃዲሾ ውይይት በቀጠናዊ ደህንነት፣ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምን እና መረጋጋትን የማስጠበቅ አስፈላጊነት ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑ ተዘግቧል፡፡…