በደቡብ አፍሪካ ሰባት ኢትዮጵያዊያን መገደላቸው ተገለጸ

በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሀገሪቱ ባጋጠመው ቀውስ ምክንያት መጎዳታቸውን ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም በደርባን አከባቢ’ ማርች ቱ ማርች ‘ በተባለ ስደተኛ ጠል አማጺ ቡድን ተደጋጋሚ ጥቃቶች በአጠቃላይ ስደተኞች ላይ ይፈፀሙ እንደነበር ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን በጁሀንስበርግ አካባቢ በኢትዮጵያውያን ላይ ያነጣጠረ ተደጋጋሚ ጥቃት እየተፈፀመ መሆኑን ተናግረዋል።

‎ካሳለፍነው መጋቢት ወር አጋማሽ ጀምሮ በተከታታይ ቀናት 2 ለረጅም ዓመታት በሀገሪቱ የኖሩና ሃብት ያፈሩ አቶ ወንድሜነህ አየለ እና አብረሃም ይመር የተባሉ ኢትዮጵያውያን በጁሀንስበርግ ጂፒ ስትሬት ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በ16 እና በ3 ጥይት ተደብድበው መገደላቸው ተገልጿል።

‎በደቡብ አፍሪካ ያሉ ኢትዮጵያውያኑ አክለውም ” ሁለቱም ግለሰቦች የኢትዮጵያውያን አስተባባሪና በኢትዮጵያና በደቡብ አፍሪካም ትልልቅ ፎቆች ያሏቸው የተከበሩ ባለሃብቶች ነበሩ ” ብለዋል።

“በነሱ ላይ በተከታታይ ቀናት መገደል በመላው ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ ስጋትን ፈጥሯል” ሲሉም አስረድተዋል።

‎ከሰሞኑን ደግሞ በተመሳሳይ በተከታታይ ቀናት ግድያ ተፈጽሟል።አንድ ቶፊቅ የተባለ ኢትዮጵያዊ በተገደለ በሁለተኛው ቀን ሌሎች ሶስት ኢትዮጵያዊያን በጥይት ተደብድበው መገደላቸውን ነዋሪዎቹ አስረድተዋል።

በደቡብ አፍሪካ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ስደተኞች ይውጡልን የሚል ዘመቻ እየተካሄደ ሲሆን ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ ስደተኞች ኢላማ ተደርገዋል።

በደቡብ አፍሪካ ለረጅም ዓመታት ከቆዩ ግለሰቦች መካከል አንድ ሰው ” ጥቃቱ የሚፈፀመው በቅጥረኛ ነብሰ ገዳዮች እንደሆነ ተናግረዋል።

ቢሆንም በአካባቢው ከአማፅያን ጋር ሕብረት የፈጠሩ ፤ በእስር ቤት ያሉ የኛ ሰዎችም አሉ ” ሲሉ አስረድተዋል።

በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን እና ራሳቸውን እንዲጠብቁ አሳስቧል።

በፕሪቶሪያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ባወጣው መግለጫ በጥቁር አፍሪካዊያን ስደተኞች ላይ ጥቃት እየተፈጸመ መሆኑን አስታውቋል።

የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ለስደተኞች ተገቢውን ጥበቃ እንዲያደርግ፣ በጉዳዩ ዙሪያ ማብራሪያ እንዲሰጠው እና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የሀገሪቱ ተቋማት ጋር ውይይት ለማድረግ መድረክ እንዲመቻችለት ጥያቄ ማቅረቡንም ኢምባሲው አስታውቋል።

በሀገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የጸጥታ ሁኔታው እስከሚረጋጋ ድረስ በቤታቸው እንዲቆዩ እና እርስ በርስ እንዲረዳዱ ጥሪ አቅርቧል።

ይሁንና እስካሁን ምን ያህል ኢትዮጵያዊያን እንደተገደሉ፣ ስለወደሙ ንብረቶች እና ሌሎች ጉዳቶች ምን ያህል እንደሆኑ በመግለጫው ላይ አልጠቀሰም።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *