Joburg

በደቡብ አፍሪካ ሰባት ኢትዮጵያዊያን መገደላቸው ተገለጸ

በደቡብ አፍሪካ ሰባት ኢትዮጵያዊያን መገደላቸው ተገለጸ

‎በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሀገሪቱ ባጋጠመው ቀውስ ምክንያት መጎዳታቸውን ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም በደርባን አከባቢ' ማርች ቱ ማርች ' በተባለ ስደተኛ ጠል አማጺ ቡድን ተደጋጋሚ ጥቃቶች በአጠቃላይ ስደተኞች ላይ ይፈፀሙ እንደነበር ነዋሪዎቹ ገልጸዋል። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን በጁሀንስበርግ አካባቢ በኢትዮጵያውያን ላይ ያነጣጠረ ተደጋጋሚ ጥቃት እየተፈፀመ መሆኑን ተናግረዋል።‎‎ካሳለፍነው መጋቢት ወር አጋማሽ ጀምሮ በተከታታይ ቀናት 2 ለረጅም ዓመታት በሀገሪቱ የኖሩና ሃብት ያፈሩ አቶ ወንድሜነህ አየለ እና አብረሃም ይመር የተባሉ ኢትዮጵያውያን በጁሀንስበርግ ጂፒ ስትሬት ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በ16 እና በ3 ጥይት ተደብድበው መገደላቸው ተገልጿል።‎‎በደቡብ አፍሪካ ያሉ ኢትዮጵያውያኑ አክለውም " ሁለቱም ግለሰቦች የኢትዮጵያውያን አስተባባሪና በኢትዮጵያና በደቡብ አፍሪካም ትልልቅ ፎቆች ያሏቸው የተከበሩ ባለሃብቶች ነበሩ " ብለዋል።…
Read More