30
Apr
በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሀገሪቱ ባጋጠመው ቀውስ ምክንያት መጎዳታቸውን ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም በደርባን አከባቢ' ማርች ቱ ማርች ' በተባለ ስደተኛ ጠል አማጺ ቡድን ተደጋጋሚ ጥቃቶች በአጠቃላይ ስደተኞች ላይ ይፈፀሙ እንደነበር ነዋሪዎቹ ገልጸዋል። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን በጁሀንስበርግ አካባቢ በኢትዮጵያውያን ላይ ያነጣጠረ ተደጋጋሚ ጥቃት እየተፈፀመ መሆኑን ተናግረዋል።ካሳለፍነው መጋቢት ወር አጋማሽ ጀምሮ በተከታታይ ቀናት 2 ለረጅም ዓመታት በሀገሪቱ የኖሩና ሃብት ያፈሩ አቶ ወንድሜነህ አየለ እና አብረሃም ይመር የተባሉ ኢትዮጵያውያን በጁሀንስበርግ ጂፒ ስትሬት ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በ16 እና በ3 ጥይት ተደብድበው መገደላቸው ተገልጿል።በደቡብ አፍሪካ ያሉ ኢትዮጵያውያኑ አክለውም " ሁለቱም ግለሰቦች የኢትዮጵያውያን አስተባባሪና በኢትዮጵያና በደቡብ አፍሪካም ትልልቅ ፎቆች ያሏቸው የተከበሩ ባለሃብቶች ነበሩ " ብለዋል።…