28
Dec
የተባበሩት መንግስታ ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የሽግግር ልዑክ (አትሚስ) የስራ ጊዜ መጠናቀቁን ተከትሎ በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የድጋፍ ተልዕኮ (አውሶም) እንዲተካው ፈቃድ ሰጥቷል፡፡ ምክር ቤቱ በትላንትናው ዕለት ባደረገው ስብሰባ አልሸባብን ለመዋጋት በሚደረገው ጥረት የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪዎች ከቀናት በኋላ አዲሱን ተልዕኮ እንዲጀምሩ ፈቅዷል፡፡ ውሳኔውን ለማጸደቅ ትላንት በተደረገው ድምጽ አሰጣጥ ላይ ከ15 አባል ሀገራት በ14ቱ ድጋፍ ያገኝ ሲሆን ለሰላም አስከባሪ ሀይሉ በሚደረገው የገንዘብ ድጋፍ ቅሬታ ያነሳቸው አሜሪካ በድምጸ ተአቅቦ ወጥታለች፡፡ ቀደም ሲል በጸደቀው የምክር ቤቱ የውሳኔ ሀሳብ መሰረት በሶማሊያ የሚሰማሩ የሰላም አስከባሪ ሀይሎችን 75 በመቶ ወጪ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደሚሸፍን ይገልጻል፡፡ በምክር ቤቱ ድምጽ መስጠት የማይችሉት ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ…