02
Dec
የአሜሪካ የታችኛው ምክር ቤት ኮንግረስ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ የአፍሪካ ጉዳዮች ንኡስ ኮሚቴ፣ ‘”በኢትዮጵያ ተስፋ ወይንስ ስጋት፣ የአሜሪካ ፖሊሲ ሁኔታ’’ ላይ ትላንት ምሸት ምስክርነት ሰምቷል፡፡ የኮሚቴው አባላት ለአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር፣ ስለ ባህር በር በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ስለተነሳው ጥያቄ የአሜሪካን አቋም ጠይቀዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ “የወደብ ጉዳይ ለኢትዮጵያ የህልውና ጉዳይ ነው” ብለው መናገራቸው በቀጠናው ካሉ አገራት አልፎ ለአሜሪካ ስጋት እንደሆነ ማይክ ሐመር ተናግረዋል። ይሁን እንጂ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የባህር በር ፍላጎት በኃይል ተፈጻሚ እንደማይሆን በይፋ እንዲሁም በግል ማረጋገጫ እንደሰጧቸው አመልክተዋል። ጥያቄው በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ስጋት እንደፈጠረ የጠቆሙት ማይክ ሐመር፣ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ የሚቀጠል ከሆነ…