04
Aug
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ምርጫ በየአራት ዓመቱ የሚካሄድ ሲሆን ላለፉት ሰባት ዓመታት የህብረቱ ሊቀመንበር የሆኑት ሙሳ ፋኪ መሃማት ስልጣን ሊጠናቀቅ አንድ ዓመት ብቻ ቀርቶታል፡፡ ይህን ተከትሎም ህብረቱ ማስታወቂያ ያወጣ ሲሆን የኬንያ ፕሬዝዳንት ለመሆን አራት ጊዜ ተወዳድረው የተሸነፉት ራይላ ኦዲንጋ በይፋ ጥያቄ አቀርበዋል፡፡ የኬንያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም የራይላ ኦዲንጋ ጥያቄን በአዲስ አበባ በይፋ ለአፍሪካ ህብረት አቅርቧል፡፡ የአፍሪካ ህብረት እጩ ተወዳዳሪዎች እንዲመዘገቡ ያስቀመጠው ጊዜ የፊታችን ማክሰኞ የሚያበቃ ሲሆን ኬንያ ራይላ ኦዲንጋን ዋነኛ እጩ አድርጋ አስመዘግባለች፡፡ ከኬንያ በተጨማሪ ጅቡቲ፣ ሲሸልስ እና ሶማሊያም እጩ ያስመዘገቡ ሲሆን ራይላ ኦዲንጋ የተሻለ ድምጽ ሊያገኙ እንደሚችሉ ተገምቷል፡፡ እጩዎች ከተመዘገቡ በኋላ ኢትዮጵያዊቷ ዲፕሎማት አምባሳደር ቆንጅት ስነጊዮርጊስ አባል የሆኑት የአፍሪካ…