15
Apr
ኢትዮጵያ ለሶስቱ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ለሱዳን ጅቡቲ እና ኬንያ የኤሌክትሪክ ሀይል በመሸጥ ላይ ስትሆን ለተጨማሪ ሀገራትም ሀይል ለመሸጥ የአዋጭነት ጥናት በማካሄድ ለይ ትገኛለች፡፡ ከአንድ ወር በፊት በታንዛኒያ ጉብኝት ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አዲ የሀይል ሽያጭ ስምምነት ተፈራርመው መመለሳቸው ይታወሳል፡፡ ኢትዮጵያ እና ኬንያ ሀምሌ 2022 ላይ ለ25 ዓመት የሚዘልቅ የሀይል ሽያጭ ስምምነት የተፈራረመች ሲሆን የሀገሪቱ ፍርድ ቤት ከዚህ በፊት የተደረጉ የሀይል ሽያጭ ስምምነቶች ሳይመረመሩ ተጨማሪ ስምምነቶች እንዳይካሄዱ እገዳ ጥሏል፡፡ ፍርድ ቤቱ በኬንያ መንግስት ላይ እገዳ ጣለው በገጠር ለሚኖረው ህዝብ እየቀረበ ያለው የኤሌክትሪክ ሀይል ታሪፍ ውድ ነው በሚል ነው፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ ለኬንያ ሀይል የምትሸጠው ኢትዮጵያ ከጠቅላላ ህዝቧ ውስጥ ግማሽ ያህሉ…