26
Apr
በሱዳን ባለው የእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት፣ ኢትዮጵያ ወደ ሀገሪቱ የምትልከው የኤሌክትሪክ ሀይል መጠን በ80 ከመቶ ያህል መቀነሱን፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል አስታውቋል፡፡ የተቋሙ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን በጉዳዩ ላይ በሰጡት መግለጫ የሱዳን የሃይል መሰረተ ልማት በጦርነቱ በመጎዳቱ የታቀደውን ያህል መጠን ሀይል መላክ አለመቻሉን ገልፀዋል፡፡ አቶ ሞገስ መኮንን እንዳሉት “ከሱዳን ጋር የተደረገው ስምምነት እስከ 100 ሜጋዋት ድረስ ለመላክ ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ ግን በመጠን ደረጃ በጣም ቀንሷል፡፡ ከ10 እስከ 20 ሜጋዋት ድረስ ነው እየላክን ያለነው፡፡ ዝቅ ሲል እስከ 10 ሜጋዋት፣ ከፍ ሲል ደግሞ እስከ 20 ሜጋዋት ይሆናል የምንልከው፡፡ ይህ የሱዳን የኤሌክትሪክ ሃይል መሰረተልማት በጦርነት በመጎዳቱ የመጣ ችግር ነው፡፡ ግጭቱ በጣም ከፍተኛ በሆነ…