11
Oct
በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ያጋጠመውን የጸጥታ ችግር ተከትሎ የመሰረታዊ ምግብ አቅርቦቶች እጥረት አጋጥሟል፤፡ የምርት እጥረት ማጋጠሙን ተከትሎም ህዝቡ በዋጋ ንረት እየተጎዳ እንደሆበነም ተገልጿል፡፡ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በከተማዋ ያጋጠመውን የሽንኩርት እጥረት ለመፍታት ከሱዳን ለማምጣት ማቀዱን አስታውቋል፡፡ ከበዓላቱ ጋር ተያይዞ የሽንኩርት ዋጋ ጭማሪ በማሳየቱ እና በየጊዜው በአትክልት ላይ ለሚደረገው የዋጋ ጭማሪ መፍትሄ ተብለው እየተሰሩ ያሉ ስራዎች መኖራቸውን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታውቋል። የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ እንደተናገሩት በመደበኛ ገበያው ላይ ለተከሰተው የዋጋ ንረት መፍትሄ ተብለው እየተሰሩ ያሉ ስራዎች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡ በተለይ የእሁድ ገበያ ላይ ከሸማች ህብረት ስራ ማህበራት ጋር በተያያዘ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ መሆኑን እና ሱዳንን ጨምሮ…