Sudancrisis

በጎንደር እና ባህርዳር ያሉ ከአንድ ሺህ በላይ ሱዳናዊያን ችግር ውስጥ መውደቃቸውን ገለጹ

በጎንደር እና ባህርዳር ያሉ ከአንድ ሺህ በላይ ሱዳናዊያን ችግር ውስጥ መውደቃቸውን ገለጹ

በአማራ ክልል በተለይም ከአንድ ሳምንት በፊት አንስቶ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት በክልሉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁ ይታወሳል፡፡ በሱዳን በተከሰተው የእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት የተሻለ ደህንነት ፍለጋ በሚል በተማ አድርገው ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ሱዳናዊያን ዜጎች ችግር ውስጥ መግባታቸውን ለአልዐይን ተናግረዋል፡፡ በተለይም በጎንደር እና በባህርዳር ባሉ ሆቴሎች የቆዩ ሱዳናዊያን በምግብ እጥረት፣ ደህንነት እና ትራንስፖርት ችግር  ገጥሞናልም ብለዋል፡፡ ቁጥራቸው ከአንድ ሺህ በላይ እንደሚሆኑ የነገሩን እነዚህ ሱዳናዊያን መንገደኞች ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ከዚያም ወደ ሳውዲ አረቢያ እና ሌሎች ሀገራት የመጓዝ አቅድን ይዘው ወደ ኢትዮጵያ እንደገቡ ተናግረዋል፡፡ ሱዳናዊያኑ በተለይም ከጎንደር እና ብህርዳር ከተሞች ውስጥ ባሉ ሆቴሎች ከተጠለሉት በተጨማሪም በመተማ በኩል አድርገው ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ከገቡ በኋላ…
Read More
የግብጽ ወታደራዊ አታቼ በሱዳን ካርቱም ተገደለ

የግብጽ ወታደራዊ አታቼ በሱዳን ካርቱም ተገደለ

በሱዳን ለ11ኛ ቀን በዘለቀው ጦርነት የሟቾች ቁጥር በየዕለቱ እየጨመረ ይገኛል። ጦርነቱ በሱዳን ብሔራዊ ጦር እና በፈጥኖ ደራሽ ሀይል መካከል ሲሆን አንዱ ባንዱ ላይ ድል መቀዳጀቱ እየተገለጸ ይገኛል። ጦርነቱ እንዲቆም በርካቶች እያሳሰቡ ቢሆንም ተፋላሚ ወገኖች ተኩስ ማቆማቸውን ቢናገሩም ጦርነቱ ግን ቆሞ አያውቅም ተብሏል። የግብጽ መንግሥት እንዳለው በሱዳን ካርቱም የነበራት ወታደራዊ አታቼ መገደሉን አስታውቃለች። ይሁንና ይህ የግብጽ ወታደራዊ አታቼ በማን እንደተገደለ እስካሁን አልተገለጸም። አሜሪካ፣ የአውሮፓ ሀገራት፣ ሳውዲ አረቢያ እና ሌሎችም ሀገራት ዲፕሎማቶቻቸውን ከሱዳን ያስወጡ ሲሆን ቀሪ ዜጎቻቸውን ግን እስካሁን አላስወጡም። በርካታ ዜጎች በካርቱም ጦርነቱ መቀጠሉን ተከትሎ በየብስ ትራንስፖርት ወደ ኢትዮጵያ ድንበር በኩል አድርገው በመውጣት ላይ እንደሆኑ ተገልጿል። ኢትዮጵያም በመተማ በኩል ከሱዳን የሚመጡ…
Read More
በሱዳን የሚገኙ አምስት ኢትዮጵያውያን መገደላቸው ተገለጸ

በሱዳን የሚገኙ አምስት ኢትዮጵያውያን መገደላቸው ተገለጸ

በሱዳን መከላከያና በፈጥኖ ደራሽ ሐይል መካከል በካርቱምእና አካባቢው የተነሳው ጦርነት በከተማዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንን ችግር ላይ እንደጣላቸው ተገልጿል። በስፍራው የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እንደነገሩን ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ችግር ላይ ናቸው። ኢትዮጵያዊያን በግለሰቦች ቤት ተጠልለው እንደሚገኙም የተገለጸ ሲሆን በተኩስ ልውውጡ የሞቱ እና የቆሰሉ መኖራቸውንም ሰምተናል። በጀነራል አቡድልፋታህ አልቡርሃን የሚመራው የሰዱን ጦር እና በጀነራል ሀምዳን ዳጋሎ ወይም ሄመቲ ሀይሎች መካከል ይፋዊ ጦርነት ሲካሄድ ዛሬ ሶስተኛ ቀኑ ላይ ይገኛል። እስካሁን በዘለቀው ጦርነት ከ100 በላይ ንጹሀን ሲገደሉ ከ600 በላይ ዜጎች ደግሞ ቆስለዋል ተብሏል። አሜሪካ፣ አውሮፓ ህብረት፣ ሩሲያ፣ ሳውዲ አረቢያ እና በርካታ የዓለማችን ሀገራት ተፋላሚ ወገኖች ጦርነት እንዲያቆሙ በማሳሰብ ላይ ናቸው። በካርቱም ያለው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ዜጎች ከቤት እንዳይወጡ እና…
Read More