09
Apr
የአማራ ክልል የማህበረሰብ ተወካዮች ሲያካሄዱት የቆየው የሀገራዊ ምክክር አጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ተጠናቋል፡፡ የአማራ ክልል የማህበረሰብ ተወካዮች ካለፈው እሁድ ጀምሮ ለአራት ተከታታይ ቀናት ሲያካሄዱት የቆየው የሀገራዊ ምክክር አጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት መጠናቁን ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ የማህበረሰብ ተወካዮቹ፤ በመጪዎቹ ቀናት ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በሚደረግ የምክክር ሂደት የሚሳተፉ 270 ወኪሎቻቸውንም መርጠዋል። በአማራ ክልል ዋና ከተማ ባህር ዳር በተካሄደው የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ከ263 ወረዳዎች የተመረጡ ከ4,500 በላይ የሚሆኑት የማህበረሰብ ተወካዮች ተሳትፈዋል፡፡ አስር የማህበረሰብ ክፍሎችን የወከሉት እነዚህ የሀገራዊ ምክክር ተሳታፊዎች፤ በባህርዳር ከተማ በነበራቸው ቆይታ ከዘጠኝ እስከ 12 አባላት በሚገኙባቸው ቡድኖች ተከፋፍለው በአበይት ክልላዊ እና ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ ሲወያዩ ቆይተዋል። ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን…