15
Nov
የሱዳን ሉአላዊ ምክርቤት ፕሬዝዳንትና የሀገሪቱ ጦር አዛዥ ጀነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን ለይፋዊ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል። ጀነራል አልቡርሃን በሱዳን ወቅታዊ ሁኔታና በሌሎች የሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ይወያያሉ ተብሏል። ሰባተኛ ወሩን የያዘው የሱዳን ጦር እና የፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ ጦርነት ከ9 ሺህ በላይ ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል። ከ5 ነጥብ 6 ሚሊየን በላይ ሰዎችን ያፈናቀለው ጦርነት በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲቆም የሚደረገው ጥረትም ቀጥሏል። ሁለቱ ሃይሎች በሪያድ በተደጋጋሚ ለድርድር ቢቀመጡም እስካሁን ከስምምነት ላይ አልደረሱም። በአዲስ አበባም በቅርቡ በሱዳን የሽግግር መንግስት ለማቋቋም ያለመና ከ80 በላይ የሀገሪቱ የፖለቲካና ሲቪል ድርጅቶች የተሳተፉበት ምክክር መደረጉ አይዘነጋም። በካርቱም የሚገኘው ኤምባሲዋ በአየር የተደበደበባት ኢትዮጵያ ከምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት…