immigrants

ኢትዮጵያ ስደተኞች ስራ እንዲቀጠሩ እና እንዲነግዱ ፈቀደች፡፡

ኢትዮጵያ ስደተኞች ስራ እንዲቀጠሩ እና እንዲነግዱ ፈቀደች፡፡

አንድ ሚሊዮን ገደማ ስደተኞችን እና ጥገኝነት ጠያቂዎችን ያስጠለለችው ኢትዮጵያ እውቅና ያገኙ ስደተኞች ስራ መቀጠር የሚያስችላቸውን መመሪያ ማዘጋጀቷን አስታውቃለች፡፡ የኢትዮጵያ ስደተኞች እና ተመላሾች አገልግሎት እንዳስታወቀው በ2011 ዓ/ም ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ስራ መቀጠርን ጨምሮ ሌሎች ጥቅሞችን እንዲያገኙ የሚያደርገው ህግ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጽደቁን አስታውቋል፡፡ ይህ አዋጅ የተደነገገውን ዕውቅና ያገኙ ስደተኞችንና ጥገኝነት ጠያቂዎችን እንዲሁም የተቀባይ ማህበረሰቦችን የኑሮ ሁኔታን ለማሻሻል እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚል የተዘጋጀ ነውም ተብሏል፡፡ የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎትም የስደተኞችን የመስራት መብት ለማስፈፀም “ስደተኞች በስራ ላይ የሚሰማሩበትን ሁኔታ ለመወሰን መመሪያ አዘጋጅቶ እንደነበር አስታውቋል፡፡ መመሪያ ቁጥር 02/2012 በሚል የተዘጋጀው ይህ ሰነድም የስደተኞች ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 1110/2010 የያዛቸውን መብቶች…
Read More
በኢትዮጵያ ከ20 ሺህ በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች በሐሰተኛ ሰነዶች እንደሚኖሩ ተገለጸ

በኢትዮጵያ ከ20 ሺህ በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች በሐሰተኛ ሰነዶች እንደሚኖሩ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት እንዳስታወቀው የውጭ ሀገር ዜጎች ሀሰተኛ ሰነዶችን ተጠቅመው ወደ ሀገር ውስጥ መግባታቸውን ደርሼበታለሁ ብሏል፡፡ የኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት በሰጡት መግለጫ በርካታ የውጭ ሀገር ዜጎች ሀሰተኛ ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ፣ ሀሰተኛ ጊዚያዊ የመኖሪያ ፈቃድ፣ ሀሰተኛ ፓስፖርት፣ ሀሰተኛ ቪዛ እና ሀሰተኛ ሰነድ አዘጋጅተው በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እየኖሩ ይገኛል ብለዋል። በተደረገው የማጣራት ስራ ከ18 ሺህ በላይ ሀሰተኛ ጊዚያዊ የመኖሪያ ፈቃድ፣ ከ1 ሺህ 500 በላይ ሀሰተኛ ቪዛ እና ከአንድ ሺህ 800 በላይ የትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያን ያሰሩ ዜጎች በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች መገኘታቸውንም ዳይሬክተሯ ተናግረዋል። በመሆኑም ህገወጥ ሰነድ ያለቸው ዜጎች ከጥር አንድ ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም…
Read More
ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ የተሰደዱ ዜጎች ቁጥር ከ60 ሺሕ በላይ ደረሰ

ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ የተሰደዱ ዜጎች ቁጥር ከ60 ሺሕ በላይ ደረሰ

በሱዳን ብሑራዊ ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ሀይል መካከል ያለውን ግጭት በመሸሽ ከ60 ሺሕ በላይ ሰዎች በአማራ፣ ቤኒሻንጉል ጉምዝ እና በጋምቤላ ክልሎች በኩል ድንበር አቋርጠው ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ገልጿል። በአጠቃላይ ወደ ኢትዮጵያ ከገቡት መካከልም ከ30 ሺሕ በላይ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ከ15 ሺሕ በላይ የሚሆኑት ሱዳናውያን ሲሆኑ፤ ከ13 ሺሕ በላይ ያህሉ ደግሞ የሌላ አገር ዜጎች መሆናቸው ተጠቁሟል። የተባበሩት መንግሥታ ድርጅት በአገሪቱ በተቀሰቀሰው ግጭት ከ25 ሚሊዮን በላይ ሰዎች አስቸኳይ የሰብአዊ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው የገለጸ ሲሆን፤ በአገሪቱ ጾታዊ ጥቃት እየጨመረ መምጣቱን አስታውቋል። እንዲሁም ጦርነቱ ከተጀመረበት ባለፈው ሚያዚያ ወር አንስቶ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መሞታቸውን፣ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውና ከግማሽ ሚሊዮን…
Read More