24
Jun
በዘንድሮ የሃጅ ጉዞ ሕይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር ከ1300 ተሻግሯል የተባለ ሲሆን ከዚህ ውስጥ አምስቱ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን ሳዑዲ አረቢያ ገልጻለች፡፡ በዘንድሮ የሃጅ ጉዞ ሕይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር ከ1ሺህ 300 መሻገሩን ሳዑዲ አረቢያ አስታውቃለች። እስካሁን በከፍተኛ ሙቀት ምክንያት የ10 ሀገራት ዜጎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን፥ 658ቱ ግብጻውያን ናቸው ተብሏል። 150 ሺህ ሃጃጆችን የላከችው ፓኪስታን 58 ዜጎቿ ህይወታቸው ማለፉን ይፋ አድርጋለች። ከ240 ሺህ ኢንዶኔዥያውያን ሃጃጆች መካከልም 183ቱ መሞታቸውን የሀገሪቱ የሃይማኖቶች ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል። የሱዳን፣ ሴኔጋል፣ ቱኒዚያ፣ ህንድ፣ ዮርዳኖስ፣ ማሌዥያና ኢራን ዜግነት ያላቸው ሃጃጆችም ህይወታቸው ማለፉን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል። ከዚህ ውስጥ አምስቱ ኢትዮጵያዊን እንደሆኑ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ገልጿል፡፡ አብዛኛዎቹ ሟቾች ያለፈቃድ…