19
Apr
ኢትዮጵያ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ዜጎቿን ወደ ሳውዲ አረቢያ ለመላክ በምልመላ ላይ እንደሆነች ተገልጿል። የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኢትዮጵያ እያደረገችው ያለው የሴቶች የጅምላ ምልመላ እንደሚያሳስባቸው ተናግረዋል ። የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች የሳውዲ አረቢያ የሰብዓዊ መብት አያያዟ ደካማ እንደሆነ ገልጸዋል። በዚህም ምክንያት ኢትዮጵያ እያደረገችው ያለው የሴት ሠራተኞች የጅምላ ምልመላ አሳሳቢ ነው ብለዋል፡፡ አሁንም ቢሆን በርካታ ኢትዮጵያዊያን ሠራተኞች በሳውዲ አረቢያ ከሠራተኛ ሕጎች የተገለሉ እና በዘመናዊ ባርነት ስርዓት ለጥቃት የተጋለጡ ናቸው ተብሏል፡፡ “ካፋላ” በተሰኘው ስርዓት አንድ ሠራተኛ በደል ቢደርስባት እና ከአሠሪዎቿ ብትሸሽ ፓስፖርቷን ጨምሮ የተለያዩ የሰነድ መረጃዎቿን እንድታጣ እንደሚደረግ እና ይህ ስርዓት አሁንም ለውጥ እንዳልተደረገበት ተገልጿል። ‹‹ሳውዲ አረቢያ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን በዘፈቀደ በማሰር እና አሰቃቂ…