05
Jun
በነዳጅ የበለጸገችው የመካከለኛው መስራቅ ሀገር ኩዌት የሦስት ወራት አስገዳጅ ስልጠና የወስዱ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞችን ለመቀበል ከመንግሥት ጋር ስምምነት ላይ መድረሷ ተገልጿል። በኢትዮጵያ እና ኩዌት መንግሥታት በኩል መግባባት ላይ መደረሱን ተከትሎም፤ በጥቂት ቀናት ውስጥ የጋራ የሥራ ስምምነት እንደሚፈረም አረብ ታይምስ ዘግቧል። ከስምምነቱ በኋላ በኢትዮጵያ የሚገኙ 600 የሚሆኑ የሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች የሰው ኃይል በማቅረብ ይሰራሉም ተብሏል፡፡ ኢትዮጵያን ሰራተኞች ቢያንስ ብቃቱ ከተረጋገጠ ተቋም የ3 ወር ስልጠና መውሰድ በግዴታ ተጥሎባቸዋል፡፡ ኩዌት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን የቤት ሰራተኞች የምታገኘው ከፊሊፒንስ ሲሆን፤ በኹለቱ አገራት መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ተከትሎ አገሪቱ የሰራተኛ እጥረት በማጋጠሙ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞችን ለመቀበል ማቀዷ ተገልጿል። የኢትዮጵያ መንግሥት ከኩዌት መንግሥት ጋር በተስማሙት መሰረት፤ አንድ ሰራተኛ በወር 90…