06
Aug
የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ሙስናን አስመልክቶ ያለውን ግንዛቤ የተመለከተ የዳሰሳ ጥናት በማካሄድ፣ የመሬትና የገቢዎች ተቋማትን ጨምሮ በበርካታ ተቋማት ውስጥ ሙስና አሳሳቢ መሆኑን ማረጋገጡን አስታውቋል። የመሬት አስተዳደርና የይዞታ ምዝገባ፣ የገቢዎችና ታክስ ጽሕፈት ቤቶች፣ የኮንስትራክሽን ፈቃድ ቁጥጥር፣ የንግድና ትራንስፖርት ቢሮዎች፣ የወረዳና የቀበሌ አስተዳደሮች በከፍተኛ ደረጃ ለሙስና ተጋላጭ መሆናቸው በጥናቱ ተለይቷል ብሏል፡፡ ኮሚሽኑ ለዳሰሳ ጥናት በተወሰደ ናሙና ከ60 በላይ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን ሙስና በማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊና በፖለቲካዊ ተግባራት ከፍተኛ እንቅፋትና ችግር የፈጠረ አሳሳቢ ችግር መሆኑን እንደነገሩት ገልጿል፡፡ በአቋራጭ የመበልፀግ ፍላጎት፣ የሥነ ምግባር ጉድለት፣ ውስብስብና ግልጽ ያልሆኑ የአገልግሎት አሰጣጥ ሒደቶችና የሕግ ማስከበር ድክመቶች ለሙስና መስፋፋት ዋነኛውንና ቀዳሚውን ድርሻ እንደሚይዙ የኮሚሽኑ የጥናት ሪፖርት ያመለክታል፡፡ በጥናቱ…