26
Jan
የደቡብ አሜሪካዋ ብራዚል ፕሬዝዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ ለይፋዊ ጉብኝት ወደ አፍሪካ እንደሚመጡ ተገልጻል። እንደ ብራዚል ዜና አገልግሎት ዘገባ ከሆነ ፕሬዝዳንት ዳ ሲልቫ የካቲት 9 ቀን 2016 ዓ.ም ወደ አዲስ አዲስ አበባ ይመጣሉ። ፕሬዝዳንት ዳ ሲልቫ በአዲስ አበባ ቆይታቸው በ37ኛው የአፍሪካ ህብረት መሪዎች ጉባኤ ላይ እንደሚሳተፉም ተገልጿል። ፕሬዝዳንት ዳ ሲልቫ ከአዲስ አበባ በተጨማሪም በግብጽ ጉብኝት እንደሚያደርጉም ተገልጿል። ከአፍሪካ በመቀጠል ከፍተኛ ቁጥር ያለው ጥቁር ህዝቦች የሚኖሩባት ብራዚል ከአፍሪካ ጋር የሚያስተሳስራት ብዙ ታሪክ አላት። ፕሬዝዳንቱ ዳ ሲልቫ ስለ ጉብኝታቸው እንዳሉት "ብራዚል ከአፍሪካ ጋር ያለባትን የታሪክ እዳ መክፈል ትፈልጋለች" ብለዋል። ለሁለተኛ ጊዜ ወደ አፍሪካ የሚጓዙት ፕሬዝዳንት ሲልቫ ከዚህ በፊት በአንጎላ፣ ኬፕ ቩርዴ እንዲሁም በሳኦቶሜ…