12
Sep
አሜሪካ አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት ድጋፍ እንደምታደርግ ገልጻለች፡፡ በተመድ የአሜሪካ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ በምክር ቤቱ አፍሪካ ሁለት ቋሚ መቀመጫዎች እና ትናንሽ የደሴት ሀገራት አንድ ተለዋዋጭ ወንበር እንዲያገኙ ግፊት እያደረግን ነው ብለዋል፡፡ ጀርመን፣ ህንድ እና ጃፓን በምክር ቤቱ ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራቸው እየጠየቁ ከሚገኙ ሀገራት መካከል ናቸው፡፡ አምባሳደሯ አፍሪካ ቋሚ ውክልና እንዲኖራት አሜሪካ እንደምትደግፍ ቢናገሩም ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት አሁን ላይ ከሚገኙት አምስት አባል ሀገራት ውጪ እንዲሰጥ ዋሽንግተን ፍላጎት እንደሌላት ገልጸዋል፡፡ በማደግ ላይ የሚገኙ ሀገራት ከፍተኛ ስልጣን ባለው የጸጥታው ምክር ቤት ውክልና እንዲኖራቸው መጠየቅ ከጀመሩ አመታት ተቆጥረዋል፡፡ ለበርካታ ጊዜያት በዚህ ጉዳይ ተደጋጋሚ ድርድር ቢደረገም ውጤታማ…