USA

አሜሪካ የ2024 ዲቪ ሎተሪ እድለኞችን ይፋ አደረገች

አሜሪካ የ2024 ዲቪ ሎተሪ እድለኞችን ይፋ አደረገች

አሜሪካ በዓለም ላይ በየዓመቱ 50 ሺህ ሰዎችን በዳይቨርሲቲ ቪዛ ወይም ዲቪ ሎተሪ አማካኝነት ወደ ሀገሯ ታስገባለች። ባሳለፍነው ጥቅምት እና ህዳር ወራት ላይ በበይነ መረብ አማካኝነት የተሞላው የ2024 ድቪ ሎተሪ አሸናፊዎች መታወቃቸው ተገልጿል። የዲቪ 2024 ማመልከቻ የሞሉ ዜጎችም መመረጣቸውን እና አለመመረጣቸውን የፊታችን ቅዳሜ ማለትም ከሚያዚያ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ማወቅ እንደሚችሉ በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ በትዊተር ገጹ ጽፏል። ኢምባሲው አክሎም በዲቪ ሎተሪ ድረገጽ ላይ በመግባት አመልካቾች ያመለከቱበትን ልዩ ቁጥር ወይም ኮድ በማስገባት ማወቅ ይችላሉም ብሏል። ይህ በዚህ እንዳለም የዲቪ ሎተሪ አሸንፋችኋል፣ ከአሜሪካ ኢምባሲ ነው እምንደውለው በሚል የሚያጭበረብሩ አካላት ስለሚኖሩ አመልካቾች እንዲጠነቀቁም አሳስቧል። ለዲቪ ሎተሪ ስለማሸነፋቸው እና አለመድረሱን አመልካቾች በራሳቸው…
Read More
ኢትዮጵያ የአሜሪካ ሰብዓዊ መብት ጥሰት ሪፖርትን ውድቅ አደረገች

ኢትዮጵያ የአሜሪካ ሰብዓዊ መብት ጥሰት ሪፖርትን ውድቅ አደረገች

ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጥሰትን በሚመለከት በአሜሪካ የወጣውን መግለጫ ውድቅ አደረገችየአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በሰሜን ኢትዮጵያ በተፈጠረው ጦርነት ሁሉም ተሳታፊዎች የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸማቸውን አስታውቋል። ዋሽንግተን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተከስቷል ሲል የደረሰችበትን ድምዳሜ የኢትዮጵያ መንግሥት በፍፁም እንደማይቀበለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ጉዳዩን በተመለከተ ያወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን እና የተመድ የሰብአዊ መብት ኮሚሽነር በጋራ ካደረጉት ምርመራ አንፃር ሲታይ ምንም አዲስ ግኝት ያልተካተተበት ነው ብሏል።  በመሆኑም የኢትዮጵያ መንግሥት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ያቀረበበትን ባዶ ውግዘት በፍፁም እንደማይቀበለው ገልጿል።  የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ያወጣው መግለጫ አንድን ወገን ብቻ…
Read More
ኢትዮጵያ ወደ አግዋ የመመለስ እድል አላት?

ኢትዮጵያ ወደ አግዋ የመመለስ እድል አላት?

በሰሜን ኢትዮጵያ በፌደራል መንግሥት እና ህወሀት መካከል ጦርነት መጀመሩን ተከትሎ ነበር አሜሪካ ኢትዮጵያን ከአሜሪካ የንግድ ችሮታ (አግዋ) እድል ያገደችው። የእግዱ ዋነኛ ምክንያትም በጦርነቱ ምክንያት በዜጎች ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እየተፈጸሙ ነው የሚል ሲሆን ኢትዮጵያ የአሜሪካንን ውሳኔ ተቃውማም ነበር። የአግዋ እድል መሰረዝ በተለይም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ባሉ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች የተቀጠሩ ዜጎችን ስራ አጥ በማድረግ በጦርነቱ ምንም አይነት ተሳትፎ የሌላቸው ኢትዮጵያዊያንን ይጎዳል ስትል ኢትዮጵያ አሜሪካ ውሳኔዋን እንድታጤነው ጠይቃም ነበር። ይሁንና ዋሸንግተን ኢትዮጵያን ከአግዋ እግድ እስካሁን ያላነሳች ሲሆን የመነሳት እድል ይኖራት ይሆን የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ነው። ጥያቄው በተለይም የጦርነቱ ዋነኛ ተሳታፊዎች የሆኑት የፌደራል መንግሥት እና ህወሀት በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት…
Read More
የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን ኢትዮጵያ ገቡ

የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን ኢትዮጵያ ገቡ

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን የአፍሪካ ጉብኝታቸውን በኢትዮጵያ ጀምረዋል። አንቶኒ ብሊንከን በአሁኑ የአፍሪካ ጉብኝታቸው ኢትዮጵያን እና ኒጀርን እንደሚጎበኙ ተገልጿል። ሚንስትሩ በአዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታ በፌደራል መንግሥት እና ህወሀት መካከል በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የተፈረመውን የሰላም ስምምነት አፈጸጸም ዙሪያ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር እንደሚመክሩ ተገልጿል። ከዚህ በተጨማሪም ከጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ፣ ከሲቪል ሶሳይቲ እና የፖለቲካ አመራሮች ጋር እንደሚመክሩም ይጠበቃል። በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት መጀመሩን ተከትሎ ግንኙነታቸው ሻክሮ የቆዩት ኢትዮጵያ እና አሜሪካ የአንቶኒ ብሊንከን ጉብኝት ለሁለቱ ሀገራት ግንኙነት መሻሻል አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ይጠበቃል። ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ባሳለፍነው ህዳር በዋሽንግተን በተካሄደው የዩኤስ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ መሳተፋቸው ይታወሳል። ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ኤርቪን ጆሴፍ ማሲንጋን በኢትዮጵያ የአሜሪካ…
Read More
አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የጣለችውን የእርዳታ እቀባ እንደምታነሳ ገለጸች

አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የጣለችውን የእርዳታ እቀባ እንደምታነሳ ገለጸች

አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የጣለችውን የፋይናንስ ድጋፍ እቀባ ልታነሳ መሆኑ ተዘገበ ለሁለት ዓመታት ሲካሄድ ቆይቶ በተያዘው ዓመት ጥቅምት ወር መቋጫ ባገኘው የፌዴራል መንግሥት እና ሕወሓት ጦርነት ከመንግሥት ጋር ቅራኔ ውስጥ ገብቶ የቆየው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ላይ ጥሎት የቆየውን የእርዳታ እና የፋይናንስ ድጋፍ እቀባ ሊያነሳ መሆኑን መስማቱን የዘገበው ፎሬን ፖሊሲ ነው፡፡ መጽሔቱ ከባለሥልጣናት ሰምቼዋለሁ ባለው መረጃ መሠረት የባይደን አስተዳደር እቀባውን ማንሳቱን በቅርቡ አዲስ አበባ ያቀናሉ በተባሉት የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ኃላፊ አንቶንዮ ብሊንክን በኩል ይፋ ያደርጋል፡፡ በሰሜኑ ጦርነት ተደጋጋሚ መግለጫዎችን ስታወጣ የቆየችውና በመንግሥት እና ሕወሓት የሠላም ስምምነት ሒደት ከፍተኛ ሚና የነበራት አሜሪካ፤ ጦርነቱ በተጀመረበት 2013 ግንቦት ወር ላይ ነበር…
Read More