ኢትዮጵያ የአሜሪካ ሰብዓዊ መብት ጥሰት ሪፖርትን ውድቅ አደረገች

ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጥሰትን በሚመለከት በአሜሪካ የወጣውን መግለጫ ውድቅ አደረገች


የአሜሪካ የውጭ ጉ
ዳይ መሥሪያ ቤት በሰሜን ኢትዮጵያ በተፈጠረው ጦርነት ሁሉም ተሳታፊዎች የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸማቸውን አስታውቋል።

ዋሽንግተን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተከስቷል ሲል የደረሰችበትን ድምዳሜ የኢትዮጵያ መንግሥት በፍፁም እንደማይቀበለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። 

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ጉዳዩን በተመለከተ ያወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን እና የተመድ የሰብአዊ መብት ኮሚሽነር በጋራ ካደረጉት ምርመራ አንፃር ሲታይ ምንም አዲስ ግኝት ያልተካተተበት ነው ብሏል። 

በመሆኑም የኢትዮጵያ መንግሥት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ያቀረበበትን ባዶ ውግዘት በፍፁም እንደማይቀበለው ገልጿል። 

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ያወጣው መግለጫ አንድን ወገን ብቻ መወንጀል ላይ ያነጣጠረ በመሆኑ እንደማይቀበለው ሚንስቴሩ ገልጿል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *