Violation

ኢትዮጵያ የአሜሪካ ሰብዓዊ መብት ጥሰት ሪፖርትን ውድቅ አደረገች

ኢትዮጵያ የአሜሪካ ሰብዓዊ መብት ጥሰት ሪፖርትን ውድቅ አደረገች

ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጥሰትን በሚመለከት በአሜሪካ የወጣውን መግለጫ ውድቅ አደረገችየአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በሰሜን ኢትዮጵያ በተፈጠረው ጦርነት ሁሉም ተሳታፊዎች የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸማቸውን አስታውቋል። ዋሽንግተን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተከስቷል ሲል የደረሰችበትን ድምዳሜ የኢትዮጵያ መንግሥት በፍፁም እንደማይቀበለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ጉዳዩን በተመለከተ ያወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን እና የተመድ የሰብአዊ መብት ኮሚሽነር በጋራ ካደረጉት ምርመራ አንፃር ሲታይ ምንም አዲስ ግኝት ያልተካተተበት ነው ብሏል።  በመሆኑም የኢትዮጵያ መንግሥት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ያቀረበበትን ባዶ ውግዘት በፍፁም እንደማይቀበለው ገልጿል።  የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ያወጣው መግለጫ አንድን ወገን ብቻ…
Read More