Anthonyblinken

የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን ኢትዮጵያ ገቡ

የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን ኢትዮጵያ ገቡ

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን የአፍሪካ ጉብኝታቸውን በኢትዮጵያ ጀምረዋል። አንቶኒ ብሊንከን በአሁኑ የአፍሪካ ጉብኝታቸው ኢትዮጵያን እና ኒጀርን እንደሚጎበኙ ተገልጿል። ሚንስትሩ በአዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታ በፌደራል መንግሥት እና ህወሀት መካከል በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የተፈረመውን የሰላም ስምምነት አፈጸጸም ዙሪያ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር እንደሚመክሩ ተገልጿል። ከዚህ በተጨማሪም ከጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ፣ ከሲቪል ሶሳይቲ እና የፖለቲካ አመራሮች ጋር እንደሚመክሩም ይጠበቃል። በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት መጀመሩን ተከትሎ ግንኙነታቸው ሻክሮ የቆዩት ኢትዮጵያ እና አሜሪካ የአንቶኒ ብሊንከን ጉብኝት ለሁለቱ ሀገራት ግንኙነት መሻሻል አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ይጠበቃል። ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ባሳለፍነው ህዳር በዋሽንግተን በተካሄደው የዩኤስ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ መሳተፋቸው ይታወሳል። ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ኤርቪን ጆሴፍ ማሲንጋን በኢትዮጵያ የአሜሪካ…
Read More