10
Mar
አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የጣለችውን የፋይናንስ ድጋፍ እቀባ ልታነሳ መሆኑ ተዘገበ ለሁለት ዓመታት ሲካሄድ ቆይቶ በተያዘው ዓመት ጥቅምት ወር መቋጫ ባገኘው የፌዴራል መንግሥት እና ሕወሓት ጦርነት ከመንግሥት ጋር ቅራኔ ውስጥ ገብቶ የቆየው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ላይ ጥሎት የቆየውን የእርዳታ እና የፋይናንስ ድጋፍ እቀባ ሊያነሳ መሆኑን መስማቱን የዘገበው ፎሬን ፖሊሲ ነው፡፡ መጽሔቱ ከባለሥልጣናት ሰምቼዋለሁ ባለው መረጃ መሠረት የባይደን አስተዳደር እቀባውን ማንሳቱን በቅርቡ አዲስ አበባ ያቀናሉ በተባሉት የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ኃላፊ አንቶንዮ ብሊንክን በኩል ይፋ ያደርጋል፡፡ በሰሜኑ ጦርነት ተደጋጋሚ መግለጫዎችን ስታወጣ የቆየችውና በመንግሥት እና ሕወሓት የሠላም ስምምነት ሒደት ከፍተኛ ሚና የነበራት አሜሪካ፤ ጦርነቱ በተጀመረበት 2013 ግንቦት ወር ላይ ነበር…