02
Feb
የተገኘው በጀት የጨርቃጨርቅና አልባሳት ኢንዱስትሪን ምርታማነት ለማሳደግ እና ለማዘመን እንደሚውል ተገልጿል፡፡ ኢትዮጵያ እና የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (ዩኒዶ) የጨርቃጨርቅና አልባሳት ኢንዱስትሪን ለማልማት የሚያስችል የ28 ሚሊየን ዶላር ሥምምነት ተፈራርመዋል። ሥምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው እና የዩኒዶ የኢትዮጵያ ተወካይ ካልባሮ አውሬሊያ ፓትሪዚያ ተፈራርመውታል። ፕሮጀክቱ በመጪዎቹ አምስት ዓመታት በኢትዮጵያ የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ልማት ኢንስቲትዩት በኩል የሚተገበር መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል። በተጨማሪም የዘርፉን ኢኮኖሚ ለማስተዋወቅና የቴክኖሎጂ ልማትን ለማሳደግ እንዲሁም የሚለቀቁ ተረፈ ምርቶችን በመቀነስ መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል የሚያስችሉ ሥራዎችን ለመተግበር እንደሚያስችልም በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል። ኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን በመሳብ ከአፍሪካ ቀዳሚ ሀገራት መካከል አንዷ የነበረች ቢሆንም ባለፉት ዓመታት ውስጥ በጦርነት ውስጥ መቆየቷ…