Prisonersexchange

ኢትዮጵያ ከቻይና፣ ብራዚል እና ደቡብ አፍሪካ ጋር የእስረኞች ልውውጥ ለማድረግ ተስማማች

ኢትዮጵያ ከቻይና፣ ብራዚል እና ደቡብ አፍሪካ ጋር የእስረኞች ልውውጥ ለማድረግ ተስማማች

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 9ኛ መደበኛ ስብሰባው በቻይና እስር ቤት ለረጅም ጊዜ በሞት ፍርድ ጥላ ስር የምትገኘውን ኢትዮጵያዊቷን ናዝራዊት አበራን ወደ ሀገሯ ለመመለስ መፍትሔ ይሰጣል የተባለለትን የፍርደኞች ማስተላለፍ ስምምነት አዋጅ አፅድቋል። ምክር ቤቱ ይህንን ስምምነት ያጸደቀው ከቻይና በተጨማሪ ከብራዚል ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ ጋር የተደረገውን የፍርደኞች ማስተላለፍ እና ከደቡብ አፍሪካ ጋር የተፈረመውን በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን አሳልፎ የመስጠት ስምምነቶችን ጨምሮ ነው። በውይይቱ ወቅት በተለይም ከቻይና ጋር የተደረገው ስምምነት ለዓመታት በፍርድ ሂደት ላይ የምትገኘውን ናዝራዊት አበራን ጉዳይ በዘላቂነት ለመፍታት ትልቅ የሕግ ማዕቀፍ እንደሚሆን ተገልጿል። ይሁን እንጂ በዕለቱ የምክር ቤት አባላት በስምምነቱ ላይ የተለያዩ አመለካከቶችን ያነሱ ሲሆን የሁለቱ ወገኖች የክርክር ነጥብም የአዋጁን አስፈላጊነትና የሉዓላዊነት…
Read More