በኢትዮጵያ ያልበለጸገ የስንዴ ዱቄት ለገበያ ማቅረብ ተከለከለ

ያልበለጸገ የስንዴ ዱቄት ማምረትም ሆነ ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት፤ ማከፋፈልም ሆነ መቸርቸር እንዲሁም እንደ ጥሬ ዕቃ መጠቀም ፈጽሞ የተከለከለ ነው ተብሏል፡፡ 

በኢትዮጵያ በህብረተሰቡ ዘንድ የሚታዩ የንጥረ-ምግብ ወይም ማይክሮ ኑትሪየንት እጥረቶችን ለመቅረፍ እና የህዝብን ጤንነት ለማረጋገጥ፣ በተወሰኑ የምግብ ምርቶች ላይ የቪታሚን እና ሚኔራል ማበልጸግ በአስገዳጅነት እንዲተገበር ተወስኗል።

በአስገዳጅነት እንዲተገበር ከተወሰኑ የምግብ ምርቶች መካከል የስንዴ ዱቄት አንዱ መሆኑን ያስተወቀው የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ሕጋዊ ግዴታዎች እና ክልከላዎች አውጥታል፡፡

የባለስልጣኑ የህዝብ እና ግንኙነት እና ኮምንኬሽን ዳይሬክተር አቶ አበራ ደመቀ እንደተናሩት አምራቾች እና አስመጪዎች ማንኛውም አካል በቪታሚን እና ሚኔራል ያልበለጸገ የስንዴ ዱቄት ማምረትም ሆነ ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት ወይም ማስመጣት በሕግ ሙሉ በሙሉ የተከለከለ እንደሆነ አንዲያውቁ አሳስበዋል፡፡

በተመሳሳይም  አከፋፋዮች እና ቸርቻሪዎች ያልበለጸገ የስንዴ ዱቄት ማከፋፈል ፣ማከማቸት ወይም ለህብረተሰቡ መቸርቸር አይቻልም ተብላል።

በሌላ በኩልም የስንዴ ዱቄትን በግብአትነት በመጠቀም ፓስታ፣ ማካሮኒ፣ ኬክ፣ ኖዱልስ፣ ዳቦ እና መሰል ምርቶችን የሚያመርቱ ተቋማትና የዳቦ ቤቶች በሙሉ በአስገዳጅነት በቪታሚን የበለጸገ የስንዴ ዱቄት ብቻ መጠቀም አለባቸው ሲሉ አቶ አበራ ጨምረው ተናረዋል።

ይህንን አስገዳጅ መመሪያ ተላልፎ የተገኘ፣ ያልበለጸገ ዱቄት የሚያመርት፣ የሚያስገባ፣ የሚያከፋፍል፣ የሚቸረችር ወይም ለምግብ ዝግጅት ምርት የሚጠቀም ማንኛውም አካል
በየደረጃው ባሉ የምግብና መድኃኒት ተቆጣጣሪ ባለስልጣናት እና የህግ አስከባሪ አካላት ጥብቅ ክትትል የሚደረግበት ሲሆን፣የምርት መያዝ መውረስ፣ የንግድ ፈቃድ ዕገዳ ወይም ሰረዛ እና አግባብ ባለው ሕግ መሠረት ሕጋዊ እርምጃ ይወሰድበታልም ተብላል።

By New admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *