03
Nov
ያልበለጸገ የስንዴ ዱቄት ማምረትም ሆነ ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት፤ ማከፋፈልም ሆነ መቸርቸር እንዲሁም እንደ ጥሬ ዕቃ መጠቀም ፈጽሞ የተከለከለ ነው ተብሏል፡፡ በኢትዮጵያ በህብረተሰቡ ዘንድ የሚታዩ የንጥረ-ምግብ ወይም ማይክሮ ኑትሪየንት እጥረቶችን ለመቅረፍ እና የህዝብን ጤንነት ለማረጋገጥ፣ በተወሰኑ የምግብ ምርቶች ላይ የቪታሚን እና ሚኔራል ማበልጸግ በአስገዳጅነት እንዲተገበር ተወስኗል። በአስገዳጅነት እንዲተገበር ከተወሰኑ የምግብ ምርቶች መካከል የስንዴ ዱቄት አንዱ መሆኑን ያስተወቀው የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ሕጋዊ ግዴታዎች እና ክልከላዎች አውጥታል፡፡ የባለስልጣኑ የህዝብ እና ግንኙነት እና ኮምንኬሽን ዳይሬክተር አቶ አበራ ደመቀ እንደተናሩት አምራቾች እና አስመጪዎች ማንኛውም አካል በቪታሚን እና ሚኔራል ያልበለጸገ የስንዴ ዱቄት ማምረትም ሆነ ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት ወይም ማስመጣት በሕግ ሙሉ በሙሉ የተከለከለ…