30
Sep
በኢትዮጵያ የሚገኙት በርካታ የቻይና ባለሃብቶች በሀገሪቱ እያጋጠመን ይገኛል ባሉት ተግዳሮቶች ወደ ጎረቤት ሀገራት እየሄዱ መሆኑን ገለፁ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ላይ ቀዳሚ የሆኑት የቻይና ባለሀብቶች እና ኩባንያዎች በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ወደ ሌሎች ሀገራት እየተሰደዱ መሆኑን ተገልጿል፡፡ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ዋነኛ ተዋናይ የሆኑት የቻይና ባለሃብቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያጋጠማቸው በመንግስት አመቺ የስራ ሁኔታዎች እየተሰጠ ባለመሆኑ ወደ ጎሮቤት ሃገራት ማለትም ወደ ኬንያ ፣ ኡጋንዳ እንዲሁም ታንዛኒያ እያማተሩ እንደሚገኙ ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል። በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ ተወካይ እንደተናገሩት በብዙ ምክንያቶች ቻይናውያን ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ያላቸውን ንግዳቸውን ወደ ጎሮቤት አገሮች አዙረዋል ። "ይህ ለኤምባሲው ብቻ ሳይሆን ለሀገርም ትልቅ ስጋት ነዉ ምክንያቱም የእኛ ተልዕኮ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለዉን ትብብር…