Loan

ኢትዮጵያ 251 ሚሊዮን ዶላር ብድር ከአይኤምኤፍ አገኘች

ኢትዮጵያ 251 ሚሊዮን ዶላር ብድር ከአይኤምኤፍ አገኘች

ዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት አይኤምኤፍ ለኢትዮጵያ 251 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ ብድር እንደሚለቅ አስታውቋል፡፡ ተቋሙ እንዳስታወቀው ብድሩን ለመልቀቅ ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ከስምምነት ላይ ደርሷል። ድርጅቱ ብድሩን ለማጽደቅ የተስማማው፣ የድርጅቱ የባለሙያዎች ቡድን ከኅዳር 3 እስከ 17 በአዲስ አበባ ተገኝቶ ኹለተኛውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ግምገማ ማድረጉን ተከትሎ ነው። የድርጅቱ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ፣ የብድር መልቀቅ ስምምነቱን በቀጣይ ሳምንታት ውስጥ እንደሚያጸድቀውና ወደፊት የኢኮኖሚ ማሻሻያ ግምገማዎች በየስድስት ወሩ እንደሚካሄዱ ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ገልጿል። የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ እጥረት እንደተቀረፈና በመደበኛውና በትይዩ የውጭ ሀገራት መገበያያ ምንዛሬዎች መካከል ያለው ልዩነት ከ10 በመቶ በታች መውረዱን የጠቀሰው ድርጅቱ፣ መንግሥት ጥብቅ የገንዘብና ፊስካል ፖሊስ እንዲቀጥል አሳስቧል። ኢትዮጵያ ካሳለፍነው ሐምሌ ወር ጀምሮ በአይኤምኤፍ እና…
Read More
የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ከ16 ቢሊዮን ዶላር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ሰጠ

የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ከ16 ቢሊዮን ዶላር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ሰጠ

የዓለም ባንክ የዳይሬክቶች ቦርድ በቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት ውስጥ ለኢትዮጵያ የ16 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ብድር እና እርዳታ እንደሚሰጥ አስታውቋል፡፡ የዓለም ባንክ በድረ ገጹ ባወጣው መግለጫው የገንዘብ ድጋፍና ብድሩ ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለውን የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃ ለመደገፍ የሚውል መሆኑን አስታውቋል። በዚህ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ካጸደቀው ገንዘብ ውስጥ 1 ቢሊዮን ዶላር ቀጥተኛ ድጋፍ መሆኑን የገለጸው ባንኩ፤ 500 ሚሊዮን ዶላሩ ደግሞ የተራዘመ ብድር ነው ብሏል። የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ እያከናወነችው ያለችውን ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ለመደገፍ በርካታ የድጋፍ ማዕቀፎችንም ይፋ አድርጓል። በዚህም መሰረት 1 ቢሊዮን ዶላር የቀጥታ እርዳታ ሲሆን 500 ሚሊዮን ዶላር የእዳ ክፍያ ማራዘሚያ እንዲሁም 320 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ትብብር በሚል…
Read More
የፓሪስ ክለብ እና ቻይና ኢትዮጵያ አዲስ ብድር እንድታገኝ ፈቀዱ

የፓሪስ ክለብ እና ቻይና ኢትዮጵያ አዲስ ብድር እንድታገኝ ፈቀዱ

በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት መቀስቀሱን ተከትሎ ነበር ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት አይኤምኤፍ ለኢትዮጵያ ሊሰጠው ያሰበውን ብድር እና እርዳታ የከለከለው፡፡ ጦርነቱ እንዲቆም ያደረገው የሰላም ስምምነት መፈረሙን ተከትሎ ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት የቆመውን ጨምሮ አዲስ ብድር እንዲሰጣት ለተቋሙ ጥያቄ ያቀረበች ቢሆንም በተደጋጋሚ የተደረጉ ውይይቶች የታሰበውን ያህል ፍሬ ሳያፈሩ ቆይተዋል፡፡ አይኤምኤፍ በድር ለኢትዮጵያ ከመፍቀዱ በፊት 20 አባላት ያሉት ፓሪስ ክለብ በመባል የሚጠራው የበለጸጉ ሀገራት ስብስብ ብድር እንዲሰጥ ይሁንታ እንዲሰጥ ሲጠበቅ ነበር፡፡ የሀገራትን ብድር የመክፈል አቅም በመገምገም ውሳኔ የሚሰጠው ይህ ስብስብ የኢትዮጵያንም አቅም ሲገመግም ቆይቶ ለአይኤምኤፍ ፈቃድ እንደሰጠ ብሉምበርግ ዘግቧል፡፡ ከፓሪስ ክለብ በተጨማሪም ሌላኛዋ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ብድር የሰጠችው ቻይና ኢትዮጵያ ከአይኤምኤፍ ተጨማሪ ብድር እንዲሰጣት ይሁንታቸውንን ሰጥተዋልም…
Read More
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብድር መስጠት አቆመ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብድር መስጠት አቆመ

በኢትዮጵያ ካሉ የንግድ ባንኮች መካከል አንጋፋ እና ሀብታም የሆነው የንግድ ባንክ ብድር መስጠቱን አቁሟል፡፡ ንግድ ባንኩ ብድር ለማግኘት የተለያዩ ሂደቶችን አልፈው ፤ ብድሩ ተፈቅዶላቸው የመልቀቅ ሂደት ላይ ያሉትም እንዲቆም ማዘዙ ተገልጿል፡፡ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ የባንኩ ደንበኛ ለኢትዮ ነጋሪ እንዳሉት የንግድ ባንክ ብድር ተፈቅዶልኝ ገንዘቡን ለመረከብ በመጠባበቅ ላይ እያለሁ ብድሩ ለጊዜው እንዲቆም መወሰኑ ተነግሮኛል ብለዋል፡፡ ሌላኛው የባንኩ ደንበኛ በበኩሉ ሶስት ሚሊዮን ብር ብድር ለመውሰድ አስፈላጊውን መስፈርቶች ሁሉ አሟልቼ ብሩ እንዲለቀቅልኝ እየተጠባበቅሁ እያለ የቅርንጫፉ ስራ አስኪጅ ደውለው ብድሩ መታገዱን ነገሩኝ ሲልም ነግሮናል፡፡   ባንኩ ብድር እንዲቆም ትእዛዝ ያስተላለፈው ከመጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ ነውም ተብሏል፡፡ ንግድ ባንኩ በጊዜያዊነት ብድር መልቀቅ…
Read More
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በሚሰጠው የብድር ወለድ ላይ ማሻሻያ አደረገ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በሚሰጠው የብድር ወለድ ላይ ማሻሻያ አደረገ

ባንኩ በግብርና ስራዎች ለተሰማሩ ተበዳሪዎች የብድር ወለድ መጠኑን ከ11 በመቶ ወደ 7 በመቶ ዝቅ ማድረጉን አስታውቋል። ባንኩ በኢትዮጵያ የግብርና ስራዎችን ለማበረታታት በሚል ለተበዳሪዎች በሚሰጠው ብድር ላይ ያስከፍል በነበረው ወለድ ምጣኔ ላይ ማሻሻያ ማድረጉን ገልጿል። የብድር ወለድ ቅናሽ የተደረገው ያ ያልታረሰን የመሬት ሀብት ወደ ስራ ለማስገባት፤ ባለሀብቶች፣ አርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች የበለጠ እንዲበረታቱ ለማድረግ በማሰብ እንደሆነ አስታውቋል። በዚህም መሰረት በአነስተኛ፣ መካከለኛና የኮርፖሬት ፕሮጀክት ብድር ለሚጠይቁ ይጠበቅ የነበረው የ11.5 በመቶ የማበደሪያ የወለድ ተመን ወደ 7 በመቶ ዝቅ አድርጓል ብሏል። ልማት ባንክ የሀገር ውስጥ ምርቶችን ለማሳደግ እና ከውጭ ተመርተው ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት በሚል የተቋቋመ የመንግስት የልማት ድርጅት…
Read More
ዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ 400 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገ

ዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ 400 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገ

ኢትዮጵያና የአለም ባንክ ለሰው ሀብት ልማት አገልግሎት የሚውል የ400 ሚሊዮን ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነት በበይነ መረብ በተካሄደ ሥነ-ስርዓት ተፈራርመዋል፡፡ በስምምነቱ ከተፈረመው 400 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ 350 ሚሊዮን ዶላር የልማት ድጋፍ ሲሆን 50 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ ብድር መሆኑ ታውቋል፡፡ የፋይናንስ ድጋፉ ለሰው ሀብት ልማት ማለትም የትምህርትን ጥራትንና ውጤታማነትን ለማሻሻልና የስርዓተ ምግብን አገልግሎት ለማጎልበት የሚውል ሲሆን፤ ከአገልግሎቱም በመላ አገሪቱ የሚገኙ ልጃገረዶችና ታዳጊ ወጣቶች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ የሰው ሀብት ልማት አገልግሎቱ በግጭትና ድርቅ የተጎዱ አካባቢዎችን የሚያካትት ሲሆን፤ የማህበራዊ አገልግሎቶች አሰጣጥን ለማጠናከርና ተጠያቂነትን ለማስፈንም አስተዋጽዖ እንዳለው ተነግሯል፡፡ የፋይናንስ ድጋፉ ውጤታማ የመማር ማስተማር ሂደትን ለማረጋጋጥ የሚያግዝ ከመሆኑም በላይ በተመረጡ ወረዳዎች የስርዓተ ምግብ አገልግሎትን…
Read More
ኢትዮጵያ 12 ቢሊዮን ዶላር ብድር እንዲሰጣት ጠየቀች

ኢትዮጵያ 12 ቢሊዮን ዶላር ብድር እንዲሰጣት ጠየቀች

የኢትዮጵያ መንግስት ለሁለተኛው አገር በቀል የኢኮኖሚ ፕሮግራም ማስፈጸሚያ 12 ቢሊዮን ዶላር ብድር ጠይቋል፡፡ ብድሩ እና እርዳታው የተጠየቀው የዓለም የገንዘብ ድርጅት አይኤምኤፍ፣ ዓለም ባንክና ኢትዮጵያ ያለባትን የውጭ ዕዳ መልሶ ከማሸጋሸግ ለማግኘት እንደሆነ ተገልጿል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ተክለ ወልድ አጥናፉ ለሪፖርተር እንዳሉት ኢትዮጵያ አሁን ላይ ከአሜሪካ፣ ፈረንሣይና ሌሎች ሀገራት ጋር ያላት ግንኙነት መልካም መሆኑ ብድሩ ሊገኝ ይችላል ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ የብድር መክፈያ ጊዜ እንዲስተካከል ጠይቃለች ያሉት አማካሪው ብድሩ ድርድር ከተደረገበት በኋላ ይለቀቃል የሚል ተስፋ መኖሩንም ጠቅሰዋል፡፡ የአሜሪካ ኮንግረስ ኢትዮጵያ ላይ ጥሎት የነበረውን ገደብ እ.ኤ.አ. በጁላይ ወር መጨረሻ ላይ ያነሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ፣ ይህም ገንዘቡን ለማግኘት ጥሩ እርምጃ ይሆናልም ተብሏል፡፡ 12 ቢሊዮን…
Read More