08
Apr
በኢትዮጵያ ካሉ የንግድ ባንኮች መካከል አንጋፋ እና ሀብታም የሆነው የንግድ ባንክ ብድር መስጠቱን አቁሟል፡፡ ንግድ ባንኩ ብድር ለማግኘት የተለያዩ ሂደቶችን አልፈው ፤ ብድሩ ተፈቅዶላቸው የመልቀቅ ሂደት ላይ ያሉትም እንዲቆም ማዘዙ ተገልጿል፡፡ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ የባንኩ ደንበኛ ለኢትዮ ነጋሪ እንዳሉት የንግድ ባንክ ብድር ተፈቅዶልኝ ገንዘቡን ለመረከብ በመጠባበቅ ላይ እያለሁ ብድሩ ለጊዜው እንዲቆም መወሰኑ ተነግሮኛል ብለዋል፡፡ ሌላኛው የባንኩ ደንበኛ በበኩሉ ሶስት ሚሊዮን ብር ብድር ለመውሰድ አስፈላጊውን መስፈርቶች ሁሉ አሟልቼ ብሩ እንዲለቀቅልኝ እየተጠባበቅሁ እያለ የቅርንጫፉ ስራ አስኪጅ ደውለው ብድሩ መታገዱን ነገሩኝ ሲልም ነግሮናል፡፡ ባንኩ ብድር እንዲቆም ትእዛዝ ያስተላለፈው ከመጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ ነውም ተብሏል፡፡ ንግድ ባንኩ በጊዜያዊነት ብድር መልቀቅ…